ፍትሃዊ የባህር በር ጥያቄን ያገናዘበ ዝግጁነት በኢትዮጵያ ባህር ኃይል..

መከላከያ ሠራዊት ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ መሰናክሎችን ተሻግሮ በየትኛውም የሀገራችን ክፍል የሚሠጠውን ተልዕኮ በጀግንነት እየፈፀመ ሠላም እና ልማትን እያረጋገጠ የሚገኝ የሀገር ክብርና መከታ ነው።

የኢትዮጵያ ባህር ኃይልም የሀገር ተልዕኮ ከተሠጣቸው የመከላከያ ክፍሎች አንዱ ሲሆን የባህር ኃይል አባላት በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በንጋት ሀይቅ ላይ በመንቀሳቀስ የግድቡን ደህንነት የማረጋገጥ አኩሪ ተግባር እየፈፀሙ ይገኛሉ።

አባላቱ ተልዕኳቸውን ከሌሎች የሠራዊታችን ክፍሎች ጋር ጥምረት በመፍጠር መረጃ በመለዋወጥና በመናበብ ውጤታማ ስራዎችን እየሰሩ ሥለመሆናቸው ይናገራሉ።

የባህር ኃይል አባላቱ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ከሚፈፅሙት የዕለት ተዕለት የግዳጅ ክትትል ባሻገር የተገኘውን አጋጣሚ በመጠቀም ለውጤት የሚያበቃቸውን ሥልጠና ጨምሮ ዝግጁነትን በሁሉም መስክ የማረጋገጥ ሥራ ይተገብራሉ። ይህ ራስን ቀድሞ የማብቃት የዝግጁነት ሥራ የሀገራችንን ፍትሃዊ የባህር በር ጥያቄ ከግምት ያስገባና ለቀጣይ ተልዕኮ የሚያበቃ አቅምና ችሎታ መላበስ የሚያስችል ስለመሆኑ አባላቱ ገልፀዋል።

በየጊዜው በሚያደርጓቸው የምድር ላይ ቅኝቶች እና ዝግጁነት የማረጋገጥ ተግባራት ሊቃጡ የሚችሉ የደህንነት ስጋቶችንና ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎችን ለመግታት የሚያስችል መሆኑም ተጠቁሟል።

ወቅታዊ አጀንዳ

to
ኢንስቲትዩቱ የቀጣይ አምስት አመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄደ።
ba
ፍትሃዊ የባህር በር ጥያቄን ያገናዘበ ዝግጁነት በኢትዮጵያ ባህር ኃይል..
a
ኢትዮጵያና አሜሪካ ታሪካዊ ግንኙነታቸውን እና ቀጠናዊ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ።
g
የመከላከያ ሚኒስትሩ MNS ጋርመንት ኢንዱስትሪን ጎበኙ።
b
በሴራና በተንኮል የባህር በር እንድናጣና የባህር ኃይላችን እንዲፈርስ መደረጉ ሀገራችንን ለተለያዩ ተግዳሮቶች ዳርጓታል።         ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ
se
በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያን ሠላም አስከባሪ ሻለቃ ወታደራዊ ዝግጁነት አረጋገጠ፡፡

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።