የማትደፈር ሀገር የማይበገር ሠራዊት” በሚል መሪ ሃሳብ 118ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን ቢሾፍቱ በሚገኘው የባህር ኃይል የስልጠና ማዕከል በተከበረበት ዕለት የበዓሉ ታዳሚዎች የተሰማቸውን ደስታና ኩራት ገልፀዋል።
በዝግጅቱ የተዳሙ የሠራዊት አባላትና ሲቪል ሰራተኞች መከላከያ ሠራዊታችን ሀገሩን በመስዋዕትነት እያፀና በድርብ ድል ታጅቦ የዛሬው ቀን መድረሱ የሚያኮራና የሚያስደስት መሆኑን ተናግረዋል።

ሠራዊታችን ለሀገራችን ኢትዮጵያ የከፈለው ውለታ በወርቅ ብዕር በደማቁ በታሪክ መዝገብ ላይ ሰፍሮ የሚኖር መሆኑን የገለፁት አስተያየት ሰጭዎች በቀጣይ በሌላ ድልና ሞገስ ታጅበን እንደምንገናኝ ትልቅ ተስፋ የሰነቁ መሆኑን ገልፀዋል።
ለመላው የመከላከያ ሠራዊትና ለቤተሰቦቹ እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብና ወዳጆች የእንኳን አደረሳችሁ መልክትም አስተላልፈዋል።

ዘጋቢ ማሙሸት አድነው
ፎቶግራፍ ተሰማ ኡርጌሳ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official





