በአምባሳደር ጄነራል ባጫ ደበሌ የተፃፈው ”የፀረ-ሽምቅ ውጊያ ጥበብ” መፅሐፍ ተመረቀ።

በኢትዮጵያ የጦር መኮንኖች ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስምና ልምድ ያካበቱት አምባሳደር ጄኔራል ባጫ ደበሌ በወታደራዊ ልምዳቸውና ጥልቅ ጥናት ላይ የተመሰረተውን ”የፀረ-ሽምቅ ውጊያ ጥበብ” መፅሐፋቸውን ዛሬ አስመርቀዋል።

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የፌዴራልና የክልል የፀጥታ አመራሮች ጄነራል መኮንኖች የመከላከያ የክብር አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው በመከላከያ መኮንኖች ክበብ በደማቅ ስነ-ስርዓት መፅሃፉ የተመረቀው።

የዕለቱ የክብር እንግዳ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ኢትዮጵያ የተሰነደ የፀረ ሽምቅ ውጊያ ማኑዋል የነበራት ቢሆንም የተሻሻለ እንዳልነበረ አውስተው ”የፀረ-ሽምቅ ውጊያ ጥበብ” መፅሐፍ ግን ዘመኑን የሚመጥንና ለጦር መሪዎች ማስተማሪያነት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። ጄኔራል ባጫ ደበሌ ይህንን ጠቃሚ መፅሐፍ በማበርከታቸውም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ምስጋና አቅርበዋል።

ብዙ የኛ ሀገር ጦር መሪዎች የሚፅፉት መፅሐፍ ታሪክ ላይ ያተኩራል። ”የፀረ-ሽምቅ ውጊያ ጥበብ” 
መፅሐፍ ግን ሳይንሳዊ ነው ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ  ይህንን በተግባር ያረጋገጡት ደግሞ ጄነራል ባጫ ናቸው  ብለዋል።

በ187 ገፆች የተቀነበበውና በአምስት ምዕራፎች የተከፋፈለው ”የፀረ-ሽምቅ ውጊያ ጥበብ” መፅሐፍ ስለሽምቅ ውጊያ ዳራና ልምድ የፀረ-ሽምቅ ውጊያ ዓለምአቀፍ ተሞክሮዎች የሸማቂና የአሸባሪ ቡድኖች ባህሪ የፀረ-ሽምቅ ውጊያና የፀረ-ሽምቅ ግብረ-ኃይል ዝግጅትን ምንነት የሚገልፅ ነው።

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።