የኢፌዴሪ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ለአየር መከላከል በግዳጅ አፈፃፀማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ክፍሎች እና አባላት የእውቅና እና የምስጋና መርሃ ግብር አካሂዷል።
በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ የኢትዮጵያን አየር ክልል በንቃት የሚጠብቅና ከማንኛውም ጥቃት የሚከላከል አስተማማኝ አየር መከላከል መገንባቱን አስታውቀዋል።
ታላቁ የህዳሴ ግድባችን በስኬት እንዲጠናቀቅ የምክትሉ አባላት የአየር ክልላችንን በጀግንነት በመጠበቅ ሃገርና ህዝብን ያኮራ ገድል ፈፅማችኋል በዚህም ልትኮሩ ይገባል ብለዋል።
የኢፌዴሪ አየር ኃይል ምክትል አዛዥ ለአየር መከላከል
ብርጋዲየር ጄኔራል ተሾመ ባጫ በበኩላቸው ምክትሉ የሙያተኛውን አቅም በከፍተኛ ሁኔታ በማሳደግ እና የአየር መከላከል ትጥቆችንም ዘመኑን የዋጁ በማድረግ በኩል ሰፊ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረው በቀጣይነትም የሚሰጠንን ማንኛውንም ግዳጅ ለመወጣት በከፍተኛ የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንገኛለን ነው ያሉት።
በመርሃ ግብሩ ለምክትሉ የግዳጅ አፈፃፀም ስኬት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱና ግዳጃቸውን በብቃት ለተወጡ ክፍሎች አባላትና አጋር አካላት የእውቅና እና የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቷል።
ዘጋቢ ይታያል ምህረት
ፎቶግራፍ ባጫ ለገሰ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official





