በ3ኛ ሳምንት የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ የ12:00 ሰአት ጨዋታ መቻል ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ሶስት ለአንድ በማሸነፍ የሊጉ መሪ ሆኗል።
መቻል ባለድል የሆነበትን ሶስቱን ጎሎች አጥቂው መሐመድ አበራ ሁለት አለምብርሃን ይግዛው ቀሪውን አንድ ጎል ከመረብ አሳርፈዋል።
መቻል ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሰባት እና ሶስት ተጨማሪ ጎል በመያዝ ፕሪምየርሊጉን መምራት ጀምሯል።

ውድድሩን በሀዋሳ እያደረገ የሚገኘው መቻል ካደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች ሁለቱን አሸንፎ በአንዱ አቻ በመወጣት ጥሩ ጅማሮ ላይ ይገኛል።
ቀጣይ በአራተኛ ሳምንት መቻል ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ጨዋታውን ያደርጋል ። ዘገባው ገረመው ጨሬ ነው
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
													
													
													




