ኢትዮጵያ በኛ ደም ደምቃ…

“ኢትዮጵያ በኛ ደም ደምቃ፣ በአፅማችን ፍላፅ ተማግራ፤
እንደታፈረች እንድትኖር፣ ከዘመን ዘመን ተከብራ፤
ከመሞት በላይ እንሙት፣ ደማችን ሺ ጊዜ ይፍሰስ፤
አየር አፈሯ ይባረክ፣ ምንጊዜም ስሟ ይታደስ”
እነዚህ ስንኞች በቃላት ብቻ የተገለጹ የስሜት መግለጫዎች አይደሉም።

በሰንደቅ ዓላማዋ ሥር መለዮዋን ለብሶ ቃል የሚገባው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ለሀገሩ ሉዓላዊነትና ለህዝብ ደህንነት የሚከፍለውን መስዋዕትነት የሚያስታውሱና ሰርክ የሚዘምራቸው የቃል ኪዳን መግለጫዎች ናቸው። ሠራዊቱም ይህንን ቃል በተግባሩ እያረጋገጠ ይገኛል።

የሠራዊቱ የየዕለት ተልዕኮ፣ የሀገር ፍቅርና ታማኝነት ቃሉን ከቃል በላይ አድርጎታል ። ፈተናዎች ቢበዙ፣ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢፈጠሩም ሠራዊቱ ሀገርና ህዝቡ የጣሉበትን እምነት ለመወጣት ተልዕኮውን በፅናትና በታማኝነት እየፈፀመ ይገኛል።

በታሪካችን ውስጥ ሀገራችንን ለመድፈር የተነሱ የውስጥና የውጭ ኃይሎች በርካታ ቢሆኑም፣ ኢትዮጵያውያን በጥበብ፣ በጽናት፣ በጀግንነትና በአንድነት ተሰባስበው ሀገራቸውን ጠብቀዋል። ይህ የጀግንነት ታሪክ ዛሬም በመከላከያ ሠራዊት ተልዕኮ ውስጥ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በተለያዩ ወቅቶች ሀገራችን ከፍተኛ ጫና በገጠማትና ህዝቡ ተስፋ ሊቆርጥ በተቃረበበት ሁኔታ፣ ሠራዊቱ በመስዋዕትነቱ ሀገርን ከመበታተንና ህዝብን ከመፈናቀል ለመጠበቅ ተሰልፏል። በዚህም ጽናቱንና ለሀገሩ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር በመስዋዕትነቱ አሳይቷል፤ ሀገርን ከብተና፣ ህዝብንም ከከፋ ችግር ለመጠበቅ የአንበሳውን ድርሻም ተወጥቷል።

የሠራዊቱ ተልዕኮ ግን በጦር ሜዳ ብቻ ተወስኖ የቀረ ብቻ ሳይሆን የሀገርን ሉዓላዊነት፣ የህዝብን ደህንነትና የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ለመጠበቅ የሚከፍለው ዋጋ የቃል ኪዳኑ ትርጉምና መገለጫ ነው። ይህም ሠራዊቱ በአስቸጋሪ ወቅት ከሀገርና ከህዝብ ጎን ያለማወላወል የመቆሙን ኃላፊነት ያሳያል።

ዛሬ የመከላከያ ሠራዊታችን ያደረገው መለዮ ሀገራዊ ኃላፊነትን፣ በሰንደቅ ዓላማዋ ሥር የገባው ቃል ደግሞ የመስዋዕትነት ቃል ኪዳኑን በተግባር እያሳየ መሆኑን ያሳያል። የሠራዊቱ ጀግንነትም በቃላት ሳይሆን በተልዕኮው፣ በፅናቱና ለሀገር በሚከፍለው ውድ ዋጋ ተገልጧል።

“ኢትዮጵያ በኛ ደም ደምቃ…”የሚለው ስንኝም ይህንኑ እውነት ያስታውሳል፤ የሀገርን ክብር በመስዋዕትነቱ፣ ሉዓላዊነታችንን በፅናቱ፣ ህዝብ የጣለበትን እምነት ደግሞ በተግባሩ እየጠበቀ መሆኑን ማረጋገጫ ነው።

ዘመኑ ያፈራውን ቴክኖሎጂ ህዝብን ለማሸበር፣ አንድነቱን ለመሸርሸርና የሠራዊቱን ስም ለማጠልሸት የሚጠቀሙ ባዳና ባንዳዎች እንዳሉ ሁሉ ፤ ሠራዊቱም ዘመናዊ ወታደራዊና ሌሎች ቴክኖሎጂዎችን በእውቀትና በከፍተኛ ሀላፊነት በመጠቀም የሀገርን ጥቅም፣ የህዝብን እምነትና የተቋሙን ሙያዊ ምስል ለመጠበቅ አቅሙን እያጠናከረ ይገኛል።

በዛሬው የቴክኖሎጂ ዘመን የመረጃ ደህንነት፣ የሳይበር አቅም፣ ዲጂታል መገናኛና የስትራቴጂክ ኮሙኒኬሽን ከሌሎች የዘመናዊ መከላከያ አቅሞች ጋር የሀገር ደህንነት አካል ሆነዋል።

የሀገር ጠባቂነት ታሪክ በመስዋዕትነት የተፃፈ፣ በፅናት የተጠናከረና በድል የተረጋገጠ ታሪክ ነው። ዛሬም ይህ የቃል ኪዳን መንፈስ በሠራዊቱ ተልዕኮ፣ በሙያዊ ብቃቱ፣ በቴክኖሎጂ አቅሙና ለሀገርና ለህዝብ ባለው ታማኝነት ቀጥሏል።

ስለዚህ “ኢትዮጵያ በኛ ደም ደምቃ” የሚለው ቃል የትናንትን መስዋዕትነት ብቻ የሚያወሳ ሳይሆን፣ጀግናው ሰራዊታችን ዛሬ እየፈፀመ ያለውን ተልዕኮና ነገ የሚጠበቀውን ሀላፊነት የሚያስታውስ ቃል ኪዳን ነው። የሀገር ዘብነቱንም በድርጊቱ እያረጋገጠ፣ ታሪኩን በዘመናዊ አቅሞች እያስቀጠለ የሀገርን ክብርና ሉዓላዊነት ለመጠበቅ በፅናት የቆመው ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን መገለጫዎችም ናቸው።

ወቅታዊ አጀንዳ

SELAM
ኢትዮጵያ በሶማሊያ ሰላም የማስከበር ተልዕኮዋን በውጤት እየፈፀመች መሆኑ ተገለፀ።
13595
ከሠራዊት ክፍሎች የተውጣጡ አመራሮች የሲቪል ወታደራዊ ትብብር የሙያ ተሞክሮ ሥልጠና ወሰዱ።
IMG_20260928_105435_619
የመከላከያ ሠራዊት የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራ
IMG_20260924_161610_762
የጋራ ግብረ ኃይሉ በትብብር ያዘጋጀው 7ኛው ዙር የጋራ የልምድ ልውውጥ ሥልጠና ተሠጠ።           
IMG_20260924_134438_790
ሠላም ጠል የሆነው ህገ-ወጡ ህወሃት በለኮሰው እሳት መለብለቡን የዕዙ አዛዥ ገለፁ።
IMG_20260922_212120_128
"ድል ቁርሱ" የተሰኘው በፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የወታደራዊ ሕይወት ጉዞ የሚያንፀባርቀው መጽሐፍ ተመረቀ

ስፖርት

SELAM
ኢትዮጵያ በሶማሊያ ሰላም የማስከበር ተልዕኮዋን በውጤት እየፈፀመች መሆኑ ተገለፀ።
13595
ከሠራዊት ክፍሎች የተውጣጡ አመራሮች የሲቪል ወታደራዊ ትብብር የሙያ ተሞክሮ ሥልጠና ወሰዱ።
IMG_20260928_105435_619
የመከላከያ ሠራዊት የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመራ
IMG_20260924_161610_762
የጋራ ግብረ ኃይሉ በትብብር ያዘጋጀው 7ኛው ዙር የጋራ የልምድ ልውውጥ ሥልጠና ተሠጠ።           
IMG_20260924_134438_790
ሠላም ጠል የሆነው ህገ-ወጡ ህወሃት በለኮሰው እሳት መለብለቡን የዕዙ አዛዥ ገለፁ።
IMG_20260922_212120_128
"ድል ቁርሱ" የተሰኘው በፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የወታደራዊ ሕይወት ጉዞ የሚያንፀባርቀው መጽሐፍ ተመረቀ

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።