የናይጄሪያ የጦር ኃይሎች አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ተወካይ በኤር ቫይስ ማርሻል አልፍሬድ ኦልጉባንጋ የተመራ ልዑክ በኢትዮጵያ መከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ጉብኝት አድርጓል።
በጉብኝቱ ወቅት የኢትዮጵያ መከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ አዛዥ ብርጋዲየር ጀነራል ዮሐንስ መኮንን ከናይጄሪያው አቻቸው ጋር በወታደራዊ ትምህርት፣ ሥልጠናና ተቋማዊ ትብብር ላይ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱም የሁለቱን ኮሌጆች የወዳጅነት ትስስር በማጠናከር፣ የሙያ ልምድ ልውውጥን፣ የጋራ ምርምርንና የአካዳሚክ ትብብርን በማስፋት ብቁ የወታደራዊ መሪዎችን ለማፍራት የሚያስችሉ ዕድሎች ላይ ትኩረት ተደርጓል።
የሁለቱ ኮሌጆች ትብብር የወታደራዊ አመራርን አቅም ከማሳደጉም በላይ በአፍሪካ ሰላምና ደኅንነት ላይ የጋራ አስተዋጽኦ ለማበርከት እንደሚያግዝ ተገልጿል።

የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅን አስመልክቶም የኮሌጁ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ጅብሪል ገሪሶ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በዝግጅቱ ላይ የሁለቱም ኮሌጆች አመራሮችና በኮሌጆቹ እየተማሩ የሚገኙ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ ብዙአየሁ ተሾመ
ፎቶግራፍ ብርቱካን ረጋሳ
