ኢንስቲትዩቱ ለሁለት ሳምንታት ሲሰጥ የቆየው የስርዓተ ፆታ ማማከር ስልጠና ተጠናቀቀ።

በመከላከያ ሠላም ማስከበር ማዕከል የዓለም አቀፍ ሠላም ማስከበር ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ለሁለት ሳምንታት ሲሰጥ የቆየው የስርዓተ ፆታ ማማከር (UN MGA) ስልጠና ተጠናቋል።

ከሰራዊቱ ክፍሎች ለተውጣጡ አባላት በፈረንሳይ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ የተሰጠው ይህ ስልጠና፣ በሠላም ማስከበር ተልዕኮ ውስጥ የስርዓተ ፆታ ጥበቃንና ሙያዊ ምክር አሰጣጥን ለማጠናከር ያለመ ነው ፡፡

በሰላም ማስከበር ማዕከል የዓለም አቀፍ ሠላም ማስከበር ማሰልጠኛ ኢንስቲቲዩት አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ገዛኸኝ ፍቃዱ የስልጠና ማጠቃለያ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ለሰልጣኞቹ የተማራችሁትን ወደተግባር መቀየር አለባችሁ ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።

በግጭት ወቅት ሴቶች፣ ወንዶች፣ ህፃናት እና አረጋውያን ለፆታዊ ጥቃት ተጋላጭ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ሰራዊቱ ለህዝብ ደህንነት እና ሰላም ቅድሚያ የሚሰጥ ስለሆነ ይህ ስልጠና ወሳኝ መሆኑን ተናግረው፤ ስልጠናው እንዲሳካ የፈረንሳይ መንግስት ላደረገው የገንዘብ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

በስልጠናው የመዝጊያ ስነ-ስርዓት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የፈረንሳይ ወታደራዊ አታሼ ኮሎኔል ዳይሚ ሳይፕሪ በበኩላቸው ስልጠናው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሠላም ማስከበር ተልዕኮ ለሚሰማሩ የሰራዊት አባላት ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ጠቁመዋል ።

በተለይም የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የፆታዊ ጥቃት ሲያጋጥም ተጎጂዎች ከደረሰባቸው ጉዳት እንዲያገግሙ ለማገዝ የሚያስችል አቅም እንደሚፈጥር አመላክተው፣ በስልጠናው ዝግጅት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ በማድረጋቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ወቅታዊ አጀንዳ

photo_2026-11-23_05-29-28
በእውቀት የሚመራ፣ ዘመናዊ መሣሪያዎችን የታጠቀና ቴክኖሎጂን የሚጠቀም የሜካናይዝድ ኃይል ተገንብቷል         ጄኔራል ይመር መኮነን
ymer
የሠራዊቱን የሎጂስቲክስ አቅም ለማሳደግ የትምህርት ሥርዓቱን ከቴክኖሎጂ ጋር ማስተሳሰር ይገባል፦     ጀኔራል ይመር መኮነን
tso
ኢንስቲትዩቱ ለሁለት ሳምንታት ሲሰጥ የቆየው የስርዓተ ፆታ ማማከር ስልጠና ተጠናቀቀ።
fen
የኢትዮጵያ ፈንጂ ማምከን ማዕከል በፈንጂ ማጽዳት እና ማምከን ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ አካሄደ።
fil
የሠራዊቱን የአኗኗር ሁኔታ ለማዘመን የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል፦  ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
desta
የመከላከያ መሀንዲስ ዋና መምሪያ ያስገነባቸውን የክፍለ ጦር ካምፖች በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመረቀ።

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።