በእውቀት የሚመራ፣ ዘመናዊ መሣሪያዎችን የታጠቀና ቴክኖሎጂን የሚጠቀም የሜካናይዝድ ኃይል ተገንብቷል         ጄኔራል ይመር መኮነን

የውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት ለወራት ያሰለጠናቸውን የሜካናይዝድ ምድብተኞችን እና አሽከርካሪዎችን አስመረቀ።

በዚሁ የምረቃ ስነ-ሥርዓት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የመከላከያ ትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ጄኔራል ይመር መኮነን ሀገራችን ጠላቶቻችን እንደሚያስቧት ደካማ ሀገር ሳትሆን፣ በእናት ሀገር ፍቅር ወኔ በተሞሉ ዜጎችና መሪዎች የተገነባች ብቃት ያለው የመከላከያ ሠራዊት ያላት ናት ሲሉ ገልፀዋል።

መከላከያ ሠራዊታችን አሁን ባለው ቁመና ግዳጁን በአጭር ጊዜና በአነስተኛ ኪሳራ በማንኛውም የመሬት አቀማመጥ ላይ መወጣት የሚችል፣ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች ለማስጠበቅ የሚያስችል ሙሉ ዝግጁነትና አቅም ያለው ኃይል እንደሆነም አንስተዋል።

ጄኔራል ይመር ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ በሜካናይዝድ ኃይል አደረጃጀት እና ሥልጠና የረጅም ጊዜ ልምድ ያላት ቢሆንም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ይበልጥ የተደራጀ፣ በእውቀት የሚመራ፣ ዘመናዊ መሣሪያዎችን የታጠቀና ቴክኖሎጂዎችን የሚጠቀም ጠንካራ አቅም መገንባት ተችሏል ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት የቴክኖሎጂ ውጤቶች በየቀኑ እየተፈጠሩ መሆናቸውን የጠቀሱት ጄኔራል ይመር መኮነን፤ የዘመኑ ጦርነት በቴክኖሎጂ ካልተደገፈ በስተቀር ውጤታማ ሊሆኑ እንደማይችልና ይህንን በመገንዘብ ከቴክኖሎጂው ዕድገት ጋር አብሮ ለመራመድ በየጊዜው መሰልጠን እንደሚገባ አሥገንዝበዋል።

የዛሬ ተመራቂዎች ወደ ሜካናይዝድ ኃይሉ ስትቀላቀሉ ከባድ ኃላፊነት የተሸከማችሁ መሆኑን አውቃችሁ፣ የምትታጠቁትን መሣሪያ በጥንቃቄና በእንክብካቤ በመያዝ ባገኛችሁት ሥልጠና ሀገራችሁን በታማኝነትና በቅንነት ማገልገል አለባችሁ ሲሉ ጄኔራል ይመር መኮነን አሳስበዋል።

ወቅታዊ አጀንዳ

photo_2026-11-23_05-29-28
በእውቀት የሚመራ፣ ዘመናዊ መሣሪያዎችን የታጠቀና ቴክኖሎጂን የሚጠቀም የሜካናይዝድ ኃይል ተገንብቷል         ጄኔራል ይመር መኮነን
ymer
የሠራዊቱን የሎጂስቲክስ አቅም ለማሳደግ የትምህርት ሥርዓቱን ከቴክኖሎጂ ጋር ማስተሳሰር ይገባል፦     ጀኔራል ይመር መኮነን
tso
ኢንስቲትዩቱ ለሁለት ሳምንታት ሲሰጥ የቆየው የስርዓተ ፆታ ማማከር ስልጠና ተጠናቀቀ።
fen
የኢትዮጵያ ፈንጂ ማምከን ማዕከል በፈንጂ ማጽዳት እና ማምከን ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ አካሄደ።
fil
የሠራዊቱን የአኗኗር ሁኔታ ለማዘመን የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል፦  ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
desta
የመከላከያ መሀንዲስ ዋና መምሪያ ያስገነባቸውን የክፍለ ጦር ካምፖች በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመረቀ።

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።