የሙያ ብቃትንና ዲጂታል አቅምን ማሳደግ ለተቀላጠፈ ተቋማዊ አገልግሎት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ።

በጠቅላይ መምሪያ ጠቅላላ አገልግሎት ማዕከል ለፋይናንስ፣ ለግዥና ለንብረት አስተዳደር ባለሙያዎች ለአንድ ሳምንት ሲሰጥ የቆየው የሙያ ማሻሻያና የዲጂታል አሰራር የአቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ።

በማጠቃለያው መርሃ ግብር በክብር እንግድነት የተገኙት የጠቅላይ መምሪያ ጠቅላላ አገልግሎት ማዕከል ኃላፊ ሜጀር ጄነራል አብዱ ከድር
በሰለጠነ፣ በሙያዊ ብቃት በታነጸና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ የሰው ኃይል መፍጠር የተቋማዊ አፈጻጸምን ለማሳደግ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማቀላጠፍና ወጪን ለመቆጠብ ወሳኝ መሆኑ ገልፀዋል።

ተተኪ ኃይልን ለማፍራትና ለተቋሙ የሚጠበቀውን ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ተከታታይ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ወሳኝ ሚና እንዳላቸው የገለፁት ኃላፊው ስልጠናና በቂ የሙያ ብቃት ያለው የሰው ኃይል መኖር የሥራ ወጪን ከመቀነስ ባለፈ፣ በአሰራር ሂደት የሚያጋጥሙ ክፍተቶችን በመለየትና በመፍታት ተግባራትን በተቀናጀና በተቀላጠፈ መንገድ ለማከናወን እንደሚያስችልም አስረድተዋል።

የማዕከሉ የፋይናንስ ሥራ አመራር ዳይሬክተር ኮሎኔል ግርማ ታደሰ በበኩላቸው፣ ስልጠናው በፋይናንስ፣ በግዥና በንብረት አስተዳደር ዘርፎች የተሰማሩ ባለሙያዎች ሁለገብ እውቀትና ሙያዊ ብቃት እንዲያዳብሩ፣ ከዘመኑ የቴክኖሎጂ እድገት ጋር ተላምደው ተግባራቸውን በብቃት እንዲወጡ ለማስቻል ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።

ስልጠናው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ከሳይበር ደህንነት ማእከልና ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዘርፍ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር የተሰጠ ሲሆን፣ በኤሌክትሮኒክ ግዥ (e-GP)፣ በኢንተርኔት ባንኪንግ አጠቃቀም፣ በዲጂታል የሥራ ሂደቶችና የሳይበር ጥቃቶችን አስቀድሞ በመከላከል ላይ ሰፊ የእውቀትና የተግባር ልምድ ልውውጥ ለማድረግ ያሥቻለ መሆኑን ኮሎኔል ግርማ ታደሠ አሥረድተዋል።

ወቅታዊ አጀንዳ

et we
የሙያ ብቃትንና ዲጂታል አቅምን ማሳደግ ለተቀላጠፈ ተቋማዊ አገልግሎት ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ።
ym11
የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስከብር ዘመናዊ ሠራዊት መገንባቱ ተገለፀ።
photo_2026-11-23_08-56-00
የፈንጂ አደጋ ግንዛቤ ማስጨበጫ የአሰልጣኞች ሥልጠና በኢንስቲትዩት ማሰልጠኛ ተጀመረ፦
photo_2026-11-23_05-29-28
በእውቀት የሚመራ፣ ዘመናዊ መሣሪያዎችን የታጠቀና ቴክኖሎጂን የሚጠቀም የሜካናይዝድ ኃይል ተገንብቷል         ጄኔራል ይመር መኮነን
ymer
የሠራዊቱን የሎጂስቲክስ አቅም ለማሳደግ የትምህርት ሥርዓቱን ከቴክኖሎጂ ጋር ማስተሳሰር ይገባል፦     ጀኔራል ይመር መኮነን
tso
ኢንስቲትዩቱ ለሁለት ሳምንታት ሲሰጥ የቆየው የስርዓተ ፆታ ማማከር ስልጠና ተጠናቀቀ።

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።