የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ትብብራቸውን ለማጠናከር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ (መኢኢግ) እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (ኢኢሆ) በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለውን ትስስርና ትብብር ለማጠናከር የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

በኢኢሆ ዋና መሥሪያ ቤት በተካሄደው ሥነ-ሥርዓት ስምምነቱን የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕን በመወከል የግሩፑ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ብርጋዲየር ጄኔራል ዮሃንስ ትኬሳ፣ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስን በመወከል ደግሞ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ብሩክ ታዬ ፈርመዋል።

በስምምነቱ መሠረት ሁለቱ ተቋማት በአቅርቦት ሰንሰለት ማጠናከር፣ በሰው ኃይል አቅም ግንባታ፣ በፋይናንስ ውጤታማነት፣ በምርምር፣ ፈጠራና የእውቀት አስተዳደር እንዲሁም በገበያ ትስስር ዘርፎች በጋራ ይሰራሉ። ትብብሩ የሁለቱን ተቋማት የጋራ አቅም ለሀገራዊ ልማት ለማዋል ያለመ ነው።

ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

ወቅታዊ አጀንዳ

fil
የሠራዊቱን የአኗኗር ሁኔታ ለማዘመን የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል፦  ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
desta
የመከላከያ መሀንዲስ ዋና መምሪያ ያስገነባቸውን የክፍለ ጦር ካምፖች በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመረቀ።
abdu
ኢትዮጵያ በዓለም ሠላምና ደህንነት ያላትን አስተዋፅኦ ለማሥቀጠልና ለማጠናከር ተግባራዊ እርምጃዎችን መውሰድ ይገባታል  - ሌተናል ጄኔራል አብዱረህማን እስማኤል
bju
ሉዓላዊነትንና ብሔራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ የሚችል ዘመኑን የዋጀ፣ በሙያዊ ብቃትና በቴክኖሎጂ የበቃ ሠራዊት ተገንብቷል።   ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
jb
ማዕከሉ ለተቋሙ ተልዕኮ መሳካት የሚጠበቅበትን እንደሚወጣ ተገለፀ።
7
በኢትዮጵያ 23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ግዳጅ አፈፃፅም እተማመናለሁ ።        ሜጀር ጀኔራል ጁንሁይ ው

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።