ሴት የሠራዊት አባላት በአመራር ሰጪነታቸው ብቁ መሆን እንዳለባቸው ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

በደቡብ ዕዝ አዘጋጅነት ከዕዝ ስታፍ፣ ከኮር እንዲሁም፣ ከክፍለጦር ለተውጣጡ ሴት የሠራዊት አባላት በወታደራዊ አመራርነት ሚና እና ክህሎት ብሎም በስርዓተ ፆታ አቅም ግንባታ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሥልጠና ለሁለት ቀናት ተሠጥቷል።

በስልጠናው ማጠቃለያ የተገኙት የመከላከያ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጄኔራል ሁሉአገርሽ ድረስ ወታደራዊ አመራርነት ማለት ጀግንነት፣ ሙያዊ ብቃት እና የሠራዊት እሴቶችን መላበስ መሆኑን በማንሳት ሴት የሠራዊት አባላት እነዚህን ነገሮች ለማግኘት በብቃት ፈተናዎችን መቋቋም እና ማለፍ እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።

በመከላከያ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት የስርአተ ፆታ ማካተት ቡድን መሪ ወይዘሮ አስተዋይ  ሳሙኤል ሴቶች ካለባቸው የስራ ጫና እና የበታችነት ስሜቶች መላቀቅ እንደሚገባቸው ገልፀው ወደ መሪነት ለመምጣት አስፈላጊውን ሁሉ አቅም መጨበጥ  እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። 

የደቡብ እዝ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ ኮሎኔል ፋንታነሽ ሞላ የተዘጋጀው ስልጠና ሴትነትን እና መሪነትን በመገንዘብ ቀጣይ ለሚጠብቅ የመሪነት ሚና ራስን ማብቃት እና ማዘጋጀት የሚያስችል አቅም እንደሚፈጥር በመግለፅ በክፍላቸው ግዳጅ እየተወጡ ባለበት ግዜ ከፍተኛ ጀብድ ለፈፀሙ ሴቶች ሽልማት በመሸለም የስልጠና መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

ዘጋቢ እዮብ ሰለሞን

ፎቶግራፍ አብረሀም ወርቁ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ

http://localhost/defensenew

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

http://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።