ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ማሠልጠኛ ማዕከል ለወራት ያሰለጠናቸውን መሠረታዊ ወታደሮች በዛሬው ዕለት በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ የመሠረታዊ ውትድርናን እና የመሠረታዊ ኮማንዶ ምልመላ መስፈርቶችን ያሟሉ ናቸው።

በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄነራል ሹማ አብደታ የውትድርና ሙያ የጀግንነት ስብዕና የተላበሰ ማንነትን የሚፈልግ ከመሆኑም በላይ ፈታኝ ለሆኑ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩ በፅናት መቆምን ይጠይቃል ብለዋል።

ይህ ሲሆን በሚያልፍ ህይወት የማያልፍ ታሪክን በመፃፍ በዜጎች ልብ ውስጥ በትውልድ ቅብብሎሽ ለዘለዓለም መኖር እንደሚቻልም ጀነራል መኮንኑ ገልፀዋል።

የመሠረታዊ ውትድርናን አጠናቀው የተመረቁት ወታደሮች በቀጣይ ከኮማንዶ ከአየር ወለድ ከልዩ ኃይልና ፀረ-ሽብር እንዲሁም ከሪፐብሊኩ የጥበቃ ኃይል ጋር ለመቀላቀል የሚያስችላቸውን ስልጠና በብቃት እንዲወጡም አሳስበዋል።

የልዩ ዘመቻዎች ዕዝና የሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል አመራርና አባላት ኢትዮጵያ አስቸጋሪ ሁኔታዎች በገጠሟት ጊዜ ሁሉ አለኝታነታቸውን በተግባር  ያረጋገጡ የቁርጥ ቀን ልጆች መሆናቸውንም ሌተናል ጄነራል ሹማ አብደታ ገልፀዋል።

ተመራቂዎቹ በቆይታቸው ጠንካራ የአካል ብቃት፣ የተኩስና የተለያዩ የውጊያ ስልቶችን በቀንና በሌሊት የተማሩና በልምምድ ያዳበሩ ከመሆኑም በላይ የስነ-ልቦናና የጤና ትምህርትን የቀሰሙ መሆናቸውን  የገለፁት ደግሞ የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ማሠልጠኛ ማዕከል አዛዥ ብርጋዲየር ጄነራል ቦጃ አጋ ናቸው።

ማሠልጠኛ ማዕከሉ የቅበላ አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደጉን የገለፁት ብርጋዲየር ጄነራል ቦጃ አጋ የሥልጠና መሠረተ ልማቶችን ማስፋፋት ተችሏልም ብለዋል።

ተመራቂዎች በስልጠና ቆይታቸው አሠልጣኞችና አመራሮች እነሱን ለማብቃት ላደረጉት ሁለንተናዊ ጥረት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በቀጣይ ለሚጠብቃቸው የመሠረታዊ ኮማንዶ ስልጠና ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።