ኢትዮጵያና አሜሪካ በሠላምና በፀጥታ ጉዳይ በጋራ የመስራት ልምዳቸውን አጠናክረው ይቀጥላሉ።

   ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም

የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የአሜሪካ በአፍሪካ ዕዝ አዛዥ  (አፍሪኮም)  ጀነራል ሚካሄል ላንግሌይ የተመራ ልዑክን ተቀብለው አነጋግረዋል።

አሜሪካና ኢትዮጵያ ከመቶ ዓመት በላይ ግንኙነት እንዳላቸው የገለፁት ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ  ጁላ ሁለቱ ወዳጅ ሀገራት በመከላከያ ዘርፉ በቀጣይም በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መግባባት መድረሳቸውን ገልፀዋል።

በውይይቱ በቀጠናው ባለው ሁኔታ የጋራ መግባባት የተያዘበትና በተለይም በቀይ ባህር ፣ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ በሚታዩ የፀጥታ ጉዳዮች ላይ  ለጋራ ተጠቃሚነት በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ  መስማማታቸውን ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ተናግረዋል።

የአፍሪኮም አዛዥ ጀነራል ሚካኤል ላንግለይ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድና በቀጠናው ከፍተኛ ሚና ያላት ሀገር መሆኗን  ጠቅሰው፣ በተለይም በሶማሊያ ሰላምን ለማስፈንና ሽብርተኝነትን ለመዋጋት  እያደረገች ላለው ጥረት ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል።

በውይይታቸው በቀጠናው ያለውን ሁኔታ በግልፅ  መረዳታቸውን የገለፁት ጀነራል ሚካኤል ላንግሌይ በቀጣይም በወታደራዊና በፀጥታ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ተናግረዋል።

በውይይቱ ላይ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋን ጨምሮ ከፍተኛ የኢትዮጵያና የአሜሪካ ወታደራዊ አመራሮች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ ብዙአየሁ ተሾመ

ፎቶግራፍ ገነት  አወቀ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ

http://localhost/defensenew

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

http://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።