በኦሮሚያ ክልል የምስራቅ ጉጂ ዞን በሰላም እና ፀጥታ ሥራ ላይ ለተሰማራው የመከላከያ ሠራዊት ምስጋና እና እውቅና ሰጥቷል።
የጉጂ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ብዙነህ፤ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ቡድኖች ምክንያት ሕዝብ እና የመንግሥት መዋቅር በሚፈለገው ደረጃ ለመንቀሳቀስ የሚቸገሩበት ሁኔታ እንደነበር አስታውሰዋል።
ይሁንና ዛሬ ላይ ሰላም በመስፈኑ ችግሩን እንደታሪክ ለማውራት እንድንበቃ ላደረጉ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ምስጋናችንን እናቀርባለን ብለዋል።
ለሰላም ማስፈኑ ሥራ ውድ ሕይወታቸውን ሰጥተው ቀና ብለን እንድንሄድ ላደረጉን የመከላከያ ሠራዊት አባላት ምስጋና መስጠት የሁሉም ዜጋ ሃላፊነት ነው ሲሉም ገልፀዋል።
እንደተቋም ለተከናወኑ የሰላምና ደኅንነት ጥበቃ ሥራዎች የጉጂ ሕዝብ እና አስተዳደር ለሰጠን ዕውቅና አክብሮታችን የላቀ ነው ያሉት የደቡብ ዕዝ ኮር አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ግርማ አየለ ፤ የተሰጠን እውቅና የሠራዊቱን እና የሕዝባችንን ትሥሥር የሚያጠናክር ነው ብለዋል።
ኢቢሲ እንደዘገበው ሠራዊቱ ከአካባቢው የፀጥታ አካላት እና ከማኅበረሰቡ ጋር በሠራቸው የፀጥታ ሥራዎች ተቀዛቅዞ የነበረው የመሰረተ ልማት እንቅስቃሴ አሁን ላይ በከፍተኛ ሁኔታ መነቃቃቱ ተገልጿል።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official