ሠራዊቱ ከየትኛውም አቅጣጫ ሊቃጣ የሚችል ማንኛውንም ጥቃት ለመከላከል ዝግጁ ነው።   ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም

‎የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የሰሜን ዕዝ ዝክረ ሰማዕታትን ለመዘከር በተዘጋጀው የመታሰቢያ ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው በስተላለፉት መልዕክት ሠራዊቱ ከየትኛውም አቅጣጫ በየትኛውም ጊዜ በልማታችን ፣በሰላማችን እና በብሄራዊ ጥቅማችን ላይ ሊቃጣ የሚችል ማንኛውንም ጥቃት ለመከላከል ዝግጁ  መሆኑን ገልፀዋል።

‎ከሃዲው ህወሃት መከላከያ ሠራዊት ለሀገሩ ክብር የከፈለውን መስዋዕትነት ክዶ ኢ -ሰብዓዊ በሆነ መንገድ ክብሩን አዋርዶ ከሰው ልጅ አዕምሮ በላይ የሆነ ግፍና ጭካኔ መፈፀሙን አውስተዋል።

ይህ ድርጊት መላው ሰራዊቱን እና መላው የኢትዮጵያን ህዝብ ያሳዘነ አንገት ያስደፋ ድርጊት በመሆኑ መቼም የትም እንዳይደገም መቼም አንረሳውም በሚል መሪ ቃል ቀኑ በልዩ ሁኔታ መታሰቡንም አንስተዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በፊት ኢትዮጵያ የድል ቀን እንጂ የክህደት ቀንን አክብራ አታውቅም ነበር ብለዋል።

‎ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ሰውን በዘረኝነት እና በጥላቻ ቀስቅሰው እና አነሳስተው ከጠላት ተዋግቶ ነፃ ያወጣቸውን፣ አንበጣ እያባረረ ሰብላቸውን የሚሰበስብላቸውን ህዝቤ ነው ብሎ ደክሞት ያረፈን የመከላከያ ሠራዊት በተኛበት ክህደት መፈፀማቸው በጣም ያማል ብለዋል።

‎ይህ ድርጊት በተፈፀመበት ወቅት የኢትዮጵያ ሰራዊት ተገዶ የህልውና ዘመቻ በጀመረበት እና ትግራይ ውስጥ በገባበት ወቅት አብዛኛው የትግራይ ህዝብ ሰራዊቱ እንደተበደለ እና እንደተካደ ያውቅ ስለነበር ከሰራዊቱ ጎን ይቆም እንደነበርም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አስታውሰዋል።

ዛሬም ቢሆን ይህ የከሃዲዎች ስብስብ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም ትላንትና እታገልልሃለሁ ብሎ ልጆቹን ከጉያው ነጥቆ እየወሰደ አስጨፍጭፎ ባዶውን ያስቀረውን የትግራይን ህዝብ ከመካስ ይልቅ ዳግም ለሌላ እልቂት እየተዘጋጀ እና የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመ ይገኛል ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ መላው የትግራይ ህዝብ ትላንትና የደረሰበት ግፍና መከራ ዛሬም እንዳይደገም በቃ ሊልና ራሱን ነፃ ሊያወጣ ይገባዋል ብለዋል።

ዘጋቢ ኤሊያስ ከለለኝ
ፎቶግራፍ ገነት አወቀ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
http://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።