ሠራዊቱ ኢትዮጵያን በኪነ ጥበብ እና በመስዋዕትነት ለዘመናት ገንብቷል፦    ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባየ

‎የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር የኪነ ጥበብና ስነ ጥበብ  ፈጠራ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባየ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ መክዬ መሃመድ የመከላከያ ጥናትና ምርምር ማዕከል ሀላፊ ብርጋዲየር ጀኔራል ይታያል ገላው የመከላከያ ስፖርት እና ኪነ ጥበብ ስራዎች ማዕከልን ጎብኝተዋል። 

‎በጉብኝቱ ወቅት የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር  የኪነ ጥበብ ስነ ጥበብ ፈጠራ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባየ ሠራዊቱ ለሀገሩ የሚሠዋ የሀገር ፍቅር መለያ በመሆኑ ይህን ሠራዊት የሚገልፅ የኪነ ጥበብ ስራዎች ማዕከሉ እየሠራ እንደሚገኝ በጉብኝቱ ማየታቸውን ተናግረው እንደ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ተገቢው ድጋፍ ለማዕከሉ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።

‎የመከላከያ ጥናትና ምርምር  ማዕከል ሀላፊ ብርጋዴር ጀነራል ይታያል ገላው በበኩላቸው ተዋግቶ የሚያሸንፍ ሠራዊትን ለመገንባት የመከላከያ ስፖርት እና ኪነ ጥበብ ስራዎች ማዕከል ሚና የጎላ በመሆኑ ማዕከሉ እየሠራ ያለውን ስራ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።

‎በጉብኝቱ የማዕከሉ የስራ እንቅስቃሴ እና የምስረታ ታሪክ ለክብር እንግዶች ገለፃ የተደረገ ሲሆን የክብር እንግዶችም የማዕከሉን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።