ብቃት ያላቸው ተተኪ ጀማሪ መኮንኖችን የማፍራቱ ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም

ብቃት ያላቸው ተተኪ ጀማሪ መኮንኖችን የማፍራቱ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን የሁርሶ አጭር ኮርስ ዕጩ መኮንን አዛዥ ኮሎኔል ከድር ጫጮ ተናግረዋል።

በመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ የሁርሶ አጭር ኮርስ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለመኮነንነት የሚያበቁ ስልጠናዎችን በመስጠት ብቁ ጀማሪ መኮንኖችን የማፍራቱን ጥረት አጠናክሮ መቀጠሉን የትምህርት ቤቱ አዛዥ ኮሎኔል ከድር ጫጮ ገልፀዋል ።

የአጭር ኮርስ ዕጩ መኮንን ትምህርት ቤት አዛዥ ኮሎኔል ከድር ጫጮ እንዳሉት ፣ የዕጩ መኮንኖችን የስልጠና ካሪኩለም አንዴ ብቻ ተቀርፆ የሚቀመጥ ባለመሆኑ ካሪኩለሙን በየጊዜው በማሻሻልና ጊዜውን የዋጀ  ስልጠና መሥጠት እየተቻለ ነው።

ዕጩ መኮንኖቹ ስልጠናቸውን አጠናቀው ሲወጡ የሚመሩትን ሠራዊት ማሰልጠንና ለግዳጅ ለማዘጋጀት የሚያስችል እውቀት እንዲጨብጡ ይደረጋል ያሉት አዛዡ በየትኛውም ጊዜና ሁኔታ የሚሰጣቸውን ውስብስብ ግዳጅ ሁሉ በድል የሚፈፅሙበትን ወታደራዊ ችሎታም እንዲጎናፀፉ ይደረጋል ብለዋል።

የአጭር ኮርስ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አዛዥ ኮሎኔል ከድር ሰልጣኞች በራሳቸው ጥረትና እውቀት የመሰብሰቢያ አደራሽ መገንባታቸውንም ገልፀዋል።

ሰልጣኞቹ የመማር ማስተማር ሂደቱ ምቹና የተሳለጠ እንዲሆን በግቢው ውስጥ እሳር ከመትከል ጀምሮ ግቢውን ውብ ፣ማራኪና አስደሳች ለማደረግ በፈጠራ የታገዙ የተለያዩ ስራዎችን እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በበላቸው ክንዴ

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

http://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።