የብርሸለቆ መሠረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አስመረቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መጋቢት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

የብርሸለቆ መሠረታዊ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በዛሬው ዕለት 41ኛ ዙር መሰረታዊ ወታደሮችን አሥመርቋል።

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ በክብር እንግድነት በመገኘት ሰልጣኞችን የመረቁት የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሃመድ ተሰማ ፣ የመከላከያ ሃይልን በሰው ሃይል ልማት ከዘመኑ ወታደራዊና ቴክኖሎጂያዊ ትጥቆች በመደገፍ ውጤታማ ግዳጆችን እንዲወጣ ለማስቻል ዘርፈ ብዙ ተግባራት መሠራቱን ገልፀዋል።

ውትድርና ሙያ ከሌሎች ሙያ ልዩ የሚያደርገው አንዱና ዋነኛው መንገድ ክብርና ውድ ህይወቱን ሰውቶ አገርን ማፅናት፣ ህዝብን ማገልገል የሚጠይቅ ሙያ መሆኑ እንደሆነ የገለፁት አዛዡ ይህን ሙያ በጥብቅ ዲስፕሊን

ለመፈጸም ደግሞ መስልጠን ሙያው የሚጠይቀውን እውቀት ብቃት ችሎታ መፍጠርና በስነ-ልቦና መዘጋጀት የግድ መሆኑን አሥረድተዋል።

የ41ኛ ዙር ተመራቂ መሠረታዊ ወታደሮች በውትድርና ሙያ አገራችሁንና ህዝባችሁን በፍፁም ታማኝነት ለማገልገል ፈቅዳችሁ፣ ሰልጥናችሁ ወደ ተቋሙ የተቀላቀላችሁ የጀግና ህዝብ ልጆች ስለሆናችሁ ልትኮሩ ይገባል ብለዋል፡፡

በማስልጠኛ ቆይታችሁ ያገኛችሁትን መነሻ አቅም በመጠቀም በምትመደቡበት አሃድ ከነባሩ ሠራዊት የምታገኙትን ልምድና ተሞክሮ ጨምራችሁ በየጊዜው አቅማችሁንና ብቃታችሁን በማሳደግ የሚሰጣችሁን ህገ – መንግስታዊ ተልዕኮ ሠራዊቱ የተገነባባቸውን እሴቶችና ህዝባዊ ባህሪን ተላብሳችሁ በጀግንነት፣ በታዛዥነትና በፅኑ ዲስፕሊን ልትወጡ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

በአወል መሃመድ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

http://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።