ኢንጂነር አይሻ መሃመድ በቤላሩስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተመራውን ከፍተኛ ልዑክ አነጋጋሩ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሚያዚያ 07 ቀን 2017 ዓ.ም

የኢፌዴሪ መከለከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እያደረገ ለሚገኘውና  በቤላሩስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማክሲም ሪዚሄንኮቭ የተመራውን ከፍተኛ ልዑክ በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ኢንጂነር አይሻ ከሌሎች የመከላከያ አመራሮች ጋር በመሆን ለልዑካን ቡድኑ አቀባባል ያደረጉላቸው ሲሆን በተለይም በሁለቱ አገራት መካካል በወታደራዊና ፀጥታ  ዘርፎች ትብብርን ለማስፋት  በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሯ በዚሁ ወቅት ሁለቱ አገራት የጋራ እሴት፣ ታሪክና የባህል መመሳሰል ያላቸው በመሆኑ ይህንን እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማሳደግ ኢትዮጵያ ፍላጎት እንዳላት ገልፀውላቸዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በበኩላቸው ሁለቱ አገራት በወታደራዊ ስልጠና፣ የመከላከያ ቴክኖሎጂ ልውውጥና በመሳሰሉ መስኮች ትብብርን ማሳደግ አስፈላጊ በመሆኑ ለዚሁ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በተጨማሪም በኢትዮጵያ እያደረጉት ባለው ይፋዊ የስራ ጉብኝትና ውይይት በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድንና በባህል ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችሉ ዕድሎች መኖራቸውንና እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶችም ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን መገንዘባቸውን ጠቅሰው ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል የበለጠ ጠንካራ አጋርነት እንዲኖር መንገድ የሚከፍት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ዘገባው የሚኒስቴሩ ፅህፈት ቤት ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-

sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

http://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።