የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሩዋንዳ የስራ ጉብኝት አደረጉ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሚያዚያ 07 ቀን 2017 ዓ.ም

የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እ.ኤ.አ ከኤፕሪል 13 እስከ 16 ቀን 2025 በሩዋንዳ የስራ ጉብኝት አድርገዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሩዋንዳ መከላከያ ሠራዊት ኤታማዦር ሹም ጄነራል ሙባረክ ሙጋንጋ በክብር ዘብ የታጀበ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን በሁለቱ ሀገራት መከላከያ መካከል የሁለትዮሽ የጋራ ውይይት ተካሂዷል።

በሁለትዮሽ የጋራ ውይይት ማጠቃለያ ላይ የሩዋንዳ መከላከያ ሠራዊት ኢታማዦር ሹም ጄኔራል  ሙባረክ ሙጋንጋ እ.ኤ.አ. በመጋቢት ወር 2025 በኢትዮጵያ ባደረጉት የስራ ጉብኝት ወቅት በሁለቱ አገሮች መከላከያ መካከል በተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ቀጣይ ትግበራ እና አፈፃፀም አቅጣጫ የሚያመለክት የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል።

ጉብኝቱ የረጅም ጊዜ የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር ትልቅ እንድምታ ያለው ሲሆን ሁለቱ አገራት በመከላከያ እና ሌሎች ተያያዥ ዘርፎች ላይ በአዳዲስ የትብብር መስኮች ለመሥራት እና የቀጠናውን ሰላም እና ደህንነትን ለማሳደግ ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያመላክት ነው።

ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በጉብኝታቸው ከሩዋንዳ ፕሬዝዳንት ከክቡር ፖል ካጋሜ ጋር በሁለቱ ሀገራት መከላከያ መኖር ስላለበት ግንኙነትና ትብብር በተመለከተ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፤ እንዲሁም ከሩዋንዳው መከላከያ ሚኒስትር ጁቬናል ማሪዛሙንዳ ጋርም ተነጋግረዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

http://www.facebook.com/fdredefense.official

sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

http://www.facebook.com/fdredefense.official

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

http://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።