ሠላምን በማፅናት ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው።ዶክተር ጌድዮን ጢሞቲዎስ 

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሚያዝያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶክተር ጌድዮን ጢሞቲዎስ በወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ ፣ አህጉራዊ ፣ ቀጠናዊና  ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለከፍተኛ የመከላከያ ሠራዊቱ አመራሮች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

“የመሀሉ ዘመን” በሚል ርዕስ ትንታኔ ያቀረቡት ሚኒስትሩ በሀገራችን የመጣውን ለውጥ ተከትሎ በተመዘገቡ ሁለንተናዊ ድሎች ሳንዘናጋ ለበለጠ ድል መትጋት ይገባል ብለዋል።

ታላቁን የህዳሴ ግድብ በከፍተኛ ፈተናዎች ውስጥ ገንብተን በማጠናቀቅ ሀገርና ህዝብን አንገት ከማስደፋት ለማዳን የተቻለበትና የጠላቶቻችን የተቀናጀ ሴራ ያከሸፍንበት አንዱ ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሀገራዊ ኢኮኖሚያችን ፈተናዎችን በመቋቋም በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉንም ዓለም አቀፍና ሀገራዊ መረጃዎችን በማጣቀስ አብራርተዋል።

ባለፉት ዓመታት ብዙ ሀገራት በዲፕሎማሲው መስክ በትብብር ለመስራት ፍቃደኝነታቸውን ማሳየታቸውንና ይህንን በጎ ዕድል በመጠቀም የብሄራዊ ጥቅማችን ለማሳካት ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

የሀገራችንን ብሄራዊ ጥቅም ለማረጋገጥና የባህር በር ተጠቃሚ ለመሆን ያቀረብነው ጥያቄ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ፍትሃዊ አጀንዳ ሆኖ መያዙንም ገልፀዋል።

ተለዋዋጭና ኢ-ተገማች  በሆነው ዓለም አቀፋዊና ቀጠናዊ እንቅስቃሴ ያለንን ሁለንተናዊ ዝግጁነት በማረጋገጥና የተለያዩ ስልቶችን በመንደፍ  ተጋላጭነታችንን ለመቀነስ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝም ገልፀዋል። በተከተልነው የሰላም ስምምነት የፀና  ወታደራዊ ድል ተመዝግቧል ያሉት  ዶክተር ጌድዮን ጢሞቲዎስ ፣ የሚያጋጥሙ ውስጣዊ ችግሮችን በሰላምና በይቅርታ በመፍታት በሀገርና በህዝብ ላይ የሚደርሰውን ጥፋት ለመቀነስ መንግስት እየወሰደው ያለው በሳል እርምጃ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡንም ተናግረዋል።

የሰላምን ጥሪ ባለመቀበል በሀይል ጥቅማችንን እናስከብራለን በማለት የሞከሩ የጥፋት ሀይሎች በተከተሉት የተሳሳተ ትርክትና ፖለቲካ ህዝቡ አንቅሮ እንደተፋቸውም ገልፀዋል።

የመከላከያ ሠራዊቱ ከሌሎች የፀጥታ ሀይሎች ጋር በመሆን በፅንፈኞች ላይ በወሰደው እርምጃም  ለሀገርና ለህዝብ ስጋት ከመሆን ወርደው የራሳቸውን ህልውና ለማቆየት እየተቸገሩ መምጣታቸውን አንስተዋል ።

ሠላምን ለማፅናትና ብልፅግናንን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ገልፀው ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችንም ባስመዘገባቸው ድሎች ሳይኩራራ ለበለጠ ተልዕኮ ራሱን ማዘጋጀት ይገባዋል ብለዋል። በውይይቱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላን ጨምሮ ከፍተኛ የሠራዊቱ አመራሮች ተገኝተዋል።

በብዙአየሁ ተሾመ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

http://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።