ሀገራችን የሚመጥን በትጥቅም በሰዉ ሃይልም የተደራጀ ዘመናዊ ሠራዊት ተገንብቷል። ጀኔራል አበበዉ ታደሰ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 16 ቀን 2017 ዓ.ም

የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበበዉ ታደሰ በልዩ ዘመቻዎች ዕዝ በስልጠና ላይ ለሚገኙት የሠራዊቱ አመራሮች በሃገራዊ እና ቀጠናዊ ጉዳዮችን ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም አንዳንድ ሃገራት እና አካላት የራሳቸዉን ፍላጎት ለማሟላት የዉስጥ ባንዳዎችን በመጠቀም ኢትዮጵያዊያንን በተለያየ መንገድ በመከፋፈል እና በማበጣበጥ አቅማቸዉን እናዳክማለን ብለዉ ላይሳካላቸው ይደክማሉ ብለዋል፡፡

የጭንቅላታቸዉ ሃሳብ ደርቆ ለሆዳቸዉ ያደሩ ፅንፈኞችና አሸባሪዎች ደግሞ የስልጣን ጥማቸዉን ለማርካት ለስልጣን የሚያበቃ ሃሳብና አገር የሚለዉ እሳቤ  ጠፍቶባቸዉ በጉልበት ስልጣን እናገኛለን ብለዉ ባንዳ ሆነው እንደሚለፉም አንስተዋል።

እኛ ደግሞ ብሔርም ሃይማኖትም የማይከፋፍለን የሃገራችን እድገት እና ከፍታ እንዲሁም የህዝባችን መለወጥ እና መበልፀግ ዓላማ አድርገን ጎጥን ሳይሆን ኢትዮጵያን የምናስቀድም ኢትዮጵያዊ ወታደሮች ነን ሲሉ አስገንዝበዋል።

ጀኔራል አበባው በአሁኑ ሰዓት ስልጣን የሚያዘዉ በሃሳብ የበላይነት እንጅ በጉልበት አይደለም፤ እኛ መነሻችንም መዳረሻችንም ህገ-መንግስቱ ነዉ። ይህንን መነሻ በማድረግም ህግ እና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለማስከበር አገራችን የሚመጥን በትጥቅም በሰዉ ሃይልም የተደራጀ ዘመናዊ ሠራዊት ተገንብቷል፤ እንደ ልዩ ዘመቻዎች ዕዝም በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ በርካታ ኮማንዶ እና አየር ወለድ እስፔሻል ፎርስ መገንባት ተችሏል ብለዋል።

ከሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም ጋር በተያያዘም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር በሰላም ከሚያምን

ከሁሉም ጋር በሰላማዊ መንገድ እንሰራለን፤ በጉልበት የሚመጣ ካለ ግን የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ሙሉ ዝግጁነት አለን  ሲሉ ተናግረዋል።

በመጨረሻም እኛ ታሪክ ያለን የታላቅ አገር ሠራዊት ነን ለቀጠናዉ ሰላም መስፈንም ትልቅ ድርሻ እና ሃፊነት አለብን ፤ ይህን መሰረት አድርገን ቀጠናዊ ትስስርን በማጠናከር እየሰራን ነዉ ያሉት የጦር ሃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበበዉ ታደሰ ብዛት ቁጥር ያለው ህዝብ ይዘን በሰላማዊ መንገድ የቀይ ባህርን የወደብ አማራጭ መጠቀም አለብን ማለታችንን እንደስተት ቆጠረዉት የሚንጫጩ እንዳሉም ጠቅሰዋል።

በምህረት ስመኝ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

http://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።