ሠራዊቱ አስተማማኝ የሀገር ደጀንነቱን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል   ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 08 ቀን 2017 ዓ.ም

ሠራዊቱ አስተማማኝ የሀገር ደጀንነቱን በተግባር እያረጋገጠ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ገለጹ።

የህዳሴ ኮር 3ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ” ህዳሴን በህዳሴ ኮር ” በሚል መሪ ሐሳብ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አክብሯል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፥ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአብሮነትና የብልጽግና ተምሣሌት ማሣያ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትም የህዳሴ ግድቡ አሁን የደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ ዘርፈ ብዙ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸዋል።

ሠራዊቱ ለህዳሴ ግድቡ ደህንነት መጠበቅና የአካባቢው ሰላም እንዲረጋገጥ ተልዕኮውን በብቃት በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የመከላከያ ሠራዊት የሀገር መከታ መሆኑን ጠቁመው፥ ሠራዊቱ አስተማማኝ የሀገር ደጀንነቱን እና የህዝብ አለኝታነቱን በተግባር እየተወጣ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

የክልሉ መንግስትም ሠራዊቱ ተልዕኮውን በሚገባ እንዲወጣ የሚያደርገውን ዘርፈ ብዙ አስተዋጽኦ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

በበዓሉ አከባበር ላይ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ  ኤታማዦር  ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ ፣የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፣የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ፣ የምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል መሠለ መሠረት፣ ጀነራል መኮንኖች፣ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ታድመዋል። ዘገባው የኢዜአ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ

http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።