ለጌርጌሴኖን የአእምሮ ህሙማን መረጃ እና ማገገሚያ ማዕከል ድጋፍ ተደረገ።

የመከላከያ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት  በየደረጃው የሚገኙ የተቋሙን ክፍሎች በማስተባበር በበጀት ዓመቱ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል። በዛሬው ዕለትም ከ240 በላይ ለሚሆኑ የጌርጌሴኖን ሴት የአእምሮ ህሙማን ከዋና መምሪያዎች እና ሌሎች ክፍሎች ጋር በመተባበር ድጋፍ ተደርጓል። 

የመከላከያ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጀኔራል ሁሉአገርሽ ድረስ ሠራዊቱ አቅሙ በፈቀደ መጠን ከኪሱ በማዋጣት ከ348 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የአልባሳት እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

ለሀገር ዋጋ የከፈሉ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ራሳቸውን መርዳት የተሳናቸውን ወገኖቻችንን መርዳት እና ማገዝ የሁላችንም ሀላፊነት ሊሆን ይገባል ያሉት ብርጋዲየር ጄኔራል ሁሉአገርሽ ድረስ ሌላው የማህበረሰብ ክፍልም መጥቶ ሊጎበኛቸው እና ድጋፍ ሊያደርግላቸው እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

እኛ በውትድርና ሙያችን ለሀገርና ለህዝብ ከምንከፍለው እንዲሁም ከምንሰራው የሙያ መስክ እና ከምንሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ ካለን ላይ ቀንሰን ድጋፍ ለሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎች ድጋፍ ማድረጋችን ለሌላውም አርአያ መሆን አለብን ያሉት የመከላከያ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታልና ዲያግኖስቲክ ማዕከል ሃላፊ ብርጋዲየር ጄኔራል ሽዋዬ ሃይሌ ናቸው።

የማዕከሉ መስራች ሊቀ-ህሩያን መለሰ አየለ ለተደረገው ድጋፍ ልባዊ ምስጋና አቅርበው ለሀገር መስዋዕትነት የምትከፍሉ የሀገር ምሰሶዎች መጥታችሁ ስለጎበኛችሁን እጅግ ደስ ብሎናል እናመሠግናለን ብለዋል።

ማዕከሉ በ1998 ዓ.ም በበጎ ፈቃደኞች መመስረቱን ገልፀው ጎዳና ላይ የወደቁትን በማንሳት ወደ ቀደመ ጤንነታቸው ለመመለስ እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ብዙዎቹ ከጎዳና ላይ የተነሱት ህሙማን በአሁኑ ሰዓት ከህመማቸው አገግመው ለሌሎቹ አገልግሎት እየሰጡ በማየታቸው ከመቼውም ጊዜ በላይ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል

ዘጋቢ ብርሃን እንዳየሁ

ፎቶ ግራፍ ዕፀገነት ዴቢሳ

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።