የኢትዮጵያ የባህር ሀይል የሚሰጠውን ግዳጅ ለመወጣት የሚያስችል ሁለንተናዊ ቁመና ላይ ይገኛል።     ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ

118ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን በዓል ላይ በመገኘት ንግግር  ያደረጉት የኢትዮጵያ የባህር ሀይል አዛዥ ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ ባስተላለፉት መልዕክት ፣ የለውጡ መንግስት የባህር በር አስፈላጊነት ላይ ባለው የፀና አቋም እና የመከላከያ ሰራዊቱ  ስትራቴጂ አመራሮች ባደረጉት ድጋፍና ክትትል የአንጋፋውን የኢትዮጵያ ባህር ሀይል ወደ ቀድሞ ገናና ስሙ ለመመለስ የተሰሩት ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ በየዘመናቱ የገጠሟትን ፈተናዎች በድል እየተወጣች የመጣች ታሪካዊና ቀደምት ሀገረ መንግስት መሆኗን አውስተው የባህር በር ጥያቄው  የኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ባህር ሀይሉ ራሱን ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች ፣ የተቋማት ግንባታ ከማሳደጉም ባለፈ የመነሻ የዉጊያ ትጥቆች ማሟላቱንም ተናግረዋል።

የባህር በርና ባህር ሀይል የማይነጣጠሉ መሆናቸውን የገለፁት ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ ሀገራችን ባላት ታሪክና መብት የባህር በር የማግኘት ጉዳይ የህልውና ጉዳይ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ሀገራችን የባህር በር ለማግኘት የምታደርገውን ፍትሃዊ ጥያቄ ለጋራ ተጠቃሚነት በሰጥቶ መቀበል መርህ መስራት እንደሚገባም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ዘጋቢ ብዙአየሁ ተሾመ
ፎቶግራፍ ተሠማ ኡርጌሳ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
http://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።