ህገ-ወጥ የመሳሪያ አዘዋዋሪዎች ላይ የሚደረገው ከትትል ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የካቲት 07 ቀን 2016 ዓ.ም

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ልዩ ስሙ አስጎሪ በተባለ ቦታ ህገ-ወጥ መሳሪያ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

በስፍራው የተሰማራው የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል ክፍለጦር ባደረገው የተቀናጀ ክትትል ህገ ወጥ መሳሪያው በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የክፍለጦሩ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ፍቃዱ ጥላሁን ገልፀዋል፡፡

ክፍሉ በአካባቢው ከተሰማራበት ጊዜ ጀምሮ በቀጠናው ሰላም ለማስፈን የሽብር ቡድኖችን እየተከታተለ በመደምሰስ ለአካባቢው ማህበረሰብ ሰላም ማስፈኑን ገልፀው የሽብር ቡድኑ ለጥፋት ተልዕኮ የሚጠቀምበትን የህገ-ወጥ መሳሪያ ዝውውር እና ንግድ ከምንጩ ለማድረቅ በአቅራቢዎችና በተቀባይ የጠላት ህዋሶች ላይ የሚደርገው ቁጥጥር የተሳካ ውጤት እያመጣ ይገኛል ብለዋል፡፡

ሰሞኑን በተደረገው ክትትል የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችና ሽጉጥ፣ የብሬንና ልዩ ልዩ ተተኳሾች መያዛቸውንና ህገ-ወጥ መሳሪያ የሚገበያዩበትን ገንዘብ 15.600.00 (አስራ አምስት ሺ ስድስት መቶ ብር) መያዙን አስታውቀዋል፡፡

ኮሎኔል ፍቃዱ ለዚህ ኦፕሬሽን መሳካት ትብብር ያደረጉትን የአካባቢውን ማህበረሰብ አመስግነው የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የተለመደውን ትብብር ህዝቡ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡ ዘገባው የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ነው።

ወቅታዊ አጀንዳ

p
የኢትዮጵያ ሠላም አሥከባሪ በማንኛውም አይነት ፈታኝ ሁኔታ ሳይረታ ተልዕኮውን እየተወጣ ነው፡፡   ብርጋዴር ጄኔራል ሺሺር ባራድዋጅ
m
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ከሪፖርታጅ ፕሮፐርቲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ስምምነት ተፈራረመ።
j
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ያስመዘገበውን አስደናቂ ለውጥ ይበልጥ ማጠናከር ይገባል፦    ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።