ኮሩ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና ፅንፈኛው መስርቶት የነበረውን ማከማቻ ደመሰሰ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ህዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም

በደቡብ ጎንደር ዞን በተለያዩ አካባቢዎች ፅንፈኛውን ቡድን እየደመሰሰ የሚገኘው ኮር አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ተሾመ ይመር ሀገር አፈርሳለሁ ብሎ የተነሳውን ፅንፈኛ ሀይል እያጠፋን እንገኛለን ብለዋል።

ፅንፈኛው ቤዝ መስርቶ የተለያዩ የሀገር ሀብትና ንብረት እየዘረፈ የሚያከማችበትና እራሱም የሚደበቅበት ቆማ በተባለው ስፍራ የሚገኘው ማዘዣው ሙሉ ለሙሉ ተደምስሷል ነው ያሉት።

እናት በምጥ ተይዛ ወደ ህክምና ማዕከል የምትወሰድበትን አምቡላንስ ሳይቀር ዘርፎ በመውሰድ ለዕኩይ አላማው መገልገያ ሲያደርግ እንደነበር የገለፁት አዛዡ አምቡላንሶችና የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ከህብረተሰቡ ዘርፎ ያከማቸው 49 ኩንታል እህልና ሌሎች ንብረቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል።

ብርጋዲየር ጄኔራል ተሾመ ይመር ግዳጃችንን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ህብረተሰቡ ወደ ልማት ስራው እንዲያተኩር ለማስቻል ዘመቻችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

ዘጋቢ ብርሃኑ አባተ

ፎቶግራፍ ከክፍሎች

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

https:///channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

https://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ
SS1
ከተጣሉበት በማንሳት በራስ አቅም ተሻሽለው ወደ ሀይል የገቡት ትጥቆች የተቋሙን የውጊያ አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራሉ።     ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
SSS
የሜጀር ጀኔራል ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለተቋምና ለሀገር የሚሠጠውን ጥቅም ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።
ASH
የውስጥ አቅሞችን አሟጦ በመጠቀም ለተቋማዊና ሀገራዊ ጥቅም ማዋል ይገባል።  ክብርት ኢንጅነር አይሻ መሀመድ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ