ለምንም አይነት ፈታኝ ሁኔታዎች የማይበገር ጠንካራ ሠራዊት ተገንብቷል።   ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

ግዳጁን በፅናት የሚፈፅምና በምንም አይነት ፈታኝ ሁኔታዎች የማይበገር ጠንካራ ሠራዊት ተገንብቷል ሲሉ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ተናገሩ።

ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ በሠራዊቱ የግዳጅ ቀጠና ተገኝተው ሠራዊቱን ባበረታቱበት ወቅት የኢትዮጵያን ሠላምና ዕድገት የማይሹ ቅጥረኞች በሠራዊታችን ጠንካራ ክንድ የእጃቸውን አግኝተዋል ሲሉ ተናግረዋል።

ለኢትዮጵያ ሠላም የምንከፍለው ዋጋ ያኮራናል ያሉት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ በተሳሳተ ስሌት የገመገሙን ታሪካዊ ጠላቶቻችንና ተላላኪ ባንዳዎቻቸው የሃፍረት ካባቸውን ተከናንበዋልም ብለዋል።

በኢትዮጵያና ህዝቦቿ ክብር መቼም ቢሆን እንደማንደራደር ታሪካዊ ጠላቶቻችን ጠንቅቀው ያውቁታል ያሉት አዛዡ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ለዚህም ትንኮሳ አድርገው ሠላሟን ለማደፍረስ የተፈታተኗት ሁሉ የደረሰባቸውን ውርደት ያስታውሱታልም ብለዋል።

እኛ ሁሌም አሸናፊ የምንሆነው የቆምንለትን አላማ  ጠንቅቀን ስለምናውቅና የኢትዮጵያ ወታደሮች ስለሆንን ነው ያሉት አዛዡ  ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ፅናት፣ቁርጠኝነትና አይበገሬነታችሁ የዚሁ ማረጋገጫም ነው ብለዋል።

በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆነን መጪውን ጊዜ ታሳቢ ያደረገ ወታደራዊ ዝግጁነታችንን እያረጋገጥን እንገኛለን፤ ህገመንግስታዊ ተልዕኳችንንም በፅናት እንፈፅማለን ሲሉም ተናግረዋል።

የሠራዊቱ አባላት በበኩላቸው የቀጣናውን ሠላም አሰተማማኝ ለማድረግ በርካታ ስኬታማ ተልዕኮዎችን ስንፈፅም ቆይተናል አሁንም ማንኛውንም ግዳጅና ተልዕኮ በጀግንነት ለመፈፀም እንደ ግልም ይሁን እንደ አሃድ ዝግጁነታችን ከመቼውም ጊዜ የላቀ ነው ብለዋል።

ዘገባው የአንዷለም ከፍያለው ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ

http://localhost/defensenew

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

http://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

p
የኢትዮጵያ ሠላም አሥከባሪ በማንኛውም አይነት ፈታኝ ሁኔታ ሳይረታ ተልዕኮውን እየተወጣ ነው፡፡   ብርጋዴር ጄኔራል ሺሺር ባራድዋጅ
m
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ከሪፖርታጅ ፕሮፐርቲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ስምምነት ተፈራረመ።
j
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ያስመዘገበውን አስደናቂ ለውጥ ይበልጥ ማጠናከር ይገባል፦    ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።