ሊከሰቱ የሚችሉ ስጋቶችን ከሩቅ የማስቀረትና ብሄራዊ አደጋ ቢከሰት በብቃት መቀልበስ የሚችል ሠራዊት ተገንብቷል።   ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ 

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 28 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ሠራዊቱን ፕሮፌሽናል በማድረግና በማዘመን በቀጣይ ሊከሰቱ የሚችሉ ስጋቶችን ከሩቅ የማስቀረትና ብሄራዊ አደጋ ቢከሰት በአስተማማኝ ሁኔታ መቀልበስ የሚችል አቅም ያለው ሠራዊት መገንባቱን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ገልፀዋል።

የመከላከያ አዛዥነትና ስታፍ ኮሌጅ ለ15ኛ ጊዜ በመደበኛ ኮርስ ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች አስመርቋል።

በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ለተመራቂዎቹ ሰርተ-ፊኬት ከሰጡ በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት፦ በሁለንተናዊ ዘርፉ የተለወጠ ፣ የወታደራዊ ስልትና ጥበብ የተላበሰና ኢትዮጵያን የሚመጥን የሀገር መከላከያ የመገንባት ጥረቱ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

ለሠራዊቱ የተሰጠው ሁለንተናዊ የአቅም ግንባታ ትኩረት ለተቋማዊ ዕድገታችን መሠረት ሆኖ መቀጠሉን ያወሱት ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የተቋሙን ጠንካራ የትምህርትና የስልጠና ማዕከላትን የመገንባትና የማጠናከር ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል።

በቀጣይም የአገራችንን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ  በሰው ሀብት ግንባታ መስኩ በትኩረት እንደሚሰራም ተናግረዋል።

ተመራቂ ከፍተኛ መኮንኖቹ በኮሌጁ ባገኙት እውቀት ፣ ክህሎትና አስተሳሰብ በሚሰማሩባቸው ክፍሎችም በመተግበር በአርአያነት እንዲመሩ አሳስበዋል።

ኮሌጁ እያስተማራቸው ከሚገኙ የወዳጅ ሀገር ከፍተኛ መኮንኖች የሀገራችንን ወታደራዊ ዲፕሎማሲ ለማሻሻልና የህዝባችንን ባህል ለማስተዋወቅ ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚኖርበትም ገልፀዋል።

ኮሌጁ ከሀገራችን ከፍተኛ መኮንኖች በተጨማሪ ከሰባት የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ አስራ ሶስት ከፍተኛ መኮንኖችም አስመርቋል።

በምረቃው ስነ ስርዓት ላይ ከፍተኛ የሠራዊቱ አመራሮች ፣ ዲፕሎማቶች ፣ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ፣ ወታደራዊ አታሼዎች ፣ የተመራቂ ቤተሰቦችና የኮሌጁ ማህበረሰብ ተገኝተዋል።

ዘጋቢ ብዙአየሁ ተሾመ

ወቅታዊ አጀንዳ

p
የኢትዮጵያ ሠላም አሥከባሪ በማንኛውም አይነት ፈታኝ ሁኔታ ሳይረታ ተልዕኮውን እየተወጣ ነው፡፡   ብርጋዴር ጄኔራል ሺሺር ባራድዋጅ
m
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ከሪፖርታጅ ፕሮፐርቲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ስምምነት ተፈራረመ።
j
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ያስመዘገበውን አስደናቂ ለውጥ ይበልጥ ማጠናከር ይገባል፦    ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።