ሠራዊቱ የታጠቀውን የዘመኑን ቴክኖሎጂ በወታደራዊ ኢንዱስትሪዎች በጥናትና ምርምር ማሳደግ ይገባል

‎     ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም

‎የኢፌዴሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ በ3ኛ ዙር መደበኛ ኮርስ ያሰለጠናቸውን ከፍተኛ መኮንኖች በዲፕሎማና በማስተርስ ዲግሪ ፕሮግራም በዛሬው ዕለት በደማቅ ሥነ-ሥርዓት አስመርቋል።

‎በምረቃ ሥነ- ስርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፣ አገራችን ተልዕኮውን በላቀ ብቃት መፈፀም የሚችል በእውቀትና በክህሎት  የጎለበተ ሠራዊት ያስፈልጋታል ተገንብቷልም ብለዋል።

‎ሠራዊቱ የታጠቀውን የዘመኑን ቴክኖሎጂ በወታደራዊ ኢንዱስትሪዎችና በጥናትና ምርምር በማሳደግ አዳዲስ ምርምሮችን ማዳበር እንደሚገባም አንስተዋል።

‎ተመራቂዎች በዚህ ወቅት አገራችን እያጋጠሟት ካሉ የውስጥ ግጭቶችና በቀጠናዉ ሊያጋጥሙ ከሚችሉ ትንታኔዎች በመነሳት ዝግጁነቱ የጎለበተና ሳይዋጋ ማሸነፍ የሚችል ሠራዊት ከመፍጠር አኳያ የጎላ ሚና መጫወት አለባችሁ ብለዋል።

‎አዳዲስ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ውሳኔዎችን በመወሰን ተጣጣፊነትን ማሳደግ እንደሚበጅም አመላክተዋል።

‎ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የተቋማችን አቅም ፈጣሪ አቅሞች እየጎለበቱ እንዲሄዱ የስልጠና ተቋማትን የውጊያና የውጊያ ድጋፍ አገልግሎቶችን የበለጠ ለማጠናከር ተመራቂዎች የቀሰማችሁትን እውቀት ከተቋሙ አሰራርና መመሪያዎች ጋር በማዋሃድ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ ይጠበቅባችኋል ሲሉ አሳስበዋል።

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ እታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በስልጠናው ብላጫ ውጤት ላስመዘገቡ ተመራቂ ስትራቴጂክ አመራሮች ሰርተ-ፊኬትና ሽልማት  አበርክተዋል

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ

http://localhost/defensenew

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

https://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ
SS1
ከተጣሉበት በማንሳት በራስ አቅም ተሻሽለው ወደ ሀይል የገቡት ትጥቆች የተቋሙን የውጊያ አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራሉ።     ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
SSS
የሜጀር ጀኔራል ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለተቋምና ለሀገር የሚሠጠውን ጥቅም ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።
ASH
የውስጥ አቅሞችን አሟጦ በመጠቀም ለተቋማዊና ሀገራዊ ጥቅም ማዋል ይገባል።  ክብርት ኢንጅነር አይሻ መሀመድ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ