የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም
ደቡብ ዕዝ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና አሽባሪውን የሸኔ ቡድን በመደምሰስ ማህበረሰቡ ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ ማስቻሉን የዕዙ አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ሰለሞን ኢተፋ ገልፀዋል።
የዕዙ ሠራዊት በተሰማሩባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች በከፈለው መስዋዕትነት ታላላቅ የመንግስት የልማት ስራዎች በተረጋጋ ሁኔታ እየተከናወኑና ለውጤት እየበቁ ነው ሲሉም ዋና አዛዡ ተናግረዋል።
ፕሮፌሽናል ሠራዊት ለመገንባት በርካታ ስራ መሰራቱንና በሃይማኖት እንዲሁም በብሄር አስተሳሰብ ያልተያዘ ብሎም አንድ የሆነ ኢትዮጵያዊ አመለካከት ያለው ጠንካራ ሠራዊት ተፈጥሯል ሲሉም ጄኔራል መኮንኑ አስረድተዋል።
ሠራዊቱ የሀገሪቱ የመጨረሻ ምሽግ እና ሀገሪቱን ከተለያዩ የጥፋት ቡድኖች የታደገ ነው ያሉት ሌተናል ጄኔራል ሰለሞን ኢተፋ ይህንን ጥንካሬ አስጠብቆ መቆየት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ እዮብ ሰለሞን
ፎቶግራፍ አሸናፊ ስዩም
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
http://localhost/defensenew/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official





