በማያቋርጥ የስልጠና ሂደት ያለፈ መሪ ድል አድራጊነት የዘወትር ተግባሩ ነው- ጀኔራል ጌታቸው ጉዲና

የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም

በማያቋርጥ የስልጠና ሂደት ያለፈ መሪ ድል አድራጊነት የዘወትር ተግባሩ ነው ሲሉ ጀኔራል ጌታቸው ጉዲና ገለፁ።

ጀኔራል ጌታቸው ጉዲና  ይህንን የተናገሩት ለ6ኛ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች በሚሰጠው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

ኢትዮጵያ ተጋርጦባት ከነበረው ሃገራዊ አደጋ ወጥታ ፊቷን ወደ ልማት ያዞረችው በሠራዊቱ የተከበረ መስዋዕትነትና የአላማ ፅናት መሆኑን ጀኔራል ጌታቸው ጉዲና ተናግረዋል።

ሠራዊታችን በፕሮፌሽናሊዝም መንገድ የተደራጀውም ሆነ የተዘጋጀው ለሰፈር ሃይሎች ሳይሆን በተሳሳተ ስሌት ኢትዮጵያን ለመድፈር ለሚሞክሩ የውጭ ሃይሎች ነው ያሉት ጀኔራል ጌታቸው ጉዲና ይህንን አቅም ለማሳደግ ሁለንተናዊ የአለም የጦርነት ባህሪን ግምት ውስጥ ያስገባ ሳይንሳዊ ስልጠና በተከታታይነት ለሠራዊቱ እየተሰጠ ነው ብለዋል።

እየተዋጋን መሠልጠን አንዱ የብቃታችን ማሳያ ነው ያሉት ጀኔራል መኮንኑ ለዘመኑ የሚመጥን እውቀት አስተሳሰብና ችሎታን  መላበስ አሰፈላጊ መሆኑንም አስረድተዋል።

የ6ኛ ዕዝም የማድረግ አቅሙን ወደላቀ ደረጃ በማሸጋገር ከዚህ ቀደም በነበሩ ውጊያዎች ሁሉ የድል አብሪ ኮከብ ሆኖ ተቋምና ሃገርን ማሻገር የቻለ ታሪካዊ ዕዝ ነው ያሉት ጀኔራል ጌታቸው ጉዲና አሁንም ቢሆን የውጭ ጠላቶቻችንን አጀንዳ ለማስፈፀም በሀገር ውስጥ ሌባና ፖሊስ የሚጫዎቱ የፅንፈኛና የአሸባሪ ሃይሎችን በማክሰም እየተቀዳጀ  የሚገኘውን አኩሪ ድል በቀጣይም የበለጠ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አመላክተዋል።

እነዚህ የጥፋት ሃይሎች ህገ መንግስትና ሃገርን አፍርሰን ስልጣን እይዛለሁ ከሚል ከንቱዋዊ ምኞት የዘለለ አንዳችም ገዥ ሃሳብ የሌላቸው በመሆኑ ህዝቡ ከሠራዊታችን ጎን ሆኖ እየታገላቸውም ይገኛል ብለዋል።

በደባልቅ አቤ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

https://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

as1
ኢትዮጵያ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካዊያን ለመፍታት በቁርጠኝነት እየሠራች መሆኗን የመከላከያ ሚኒስትሯ ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ገለፁ።
as
ኢትዮጵያ እና ኮንጎ ሪፐብሊክ (ብራዛቢል ) በወታደራዊ መስኮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
s6
በአምባሳደር ጄነራል ባጫ ደበሌ የተፃፈው ''የፀረ-ሽምቅ ውጊያ ጥበብ'' መፅሐፍ ተመረቀ።
mf
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች አካል መሆን እንዳለባት የፈረንሣይ የምድር ኃይል አዛዥ ጄነራል ፒየር ሺል ገለፁ።
ay3
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ከኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።
Y
ፈረንሣይ ከኢትዮጵያ ጋር በወታደራዊ መስክ የበለጠ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን የፈረንሣይ ምድር ጦር አዛዥ ጄኔራል ፒየር ሺል ገለፁ።

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ