በክልሉ የተገኘው ሠላም የሠራዊታችን ክቡር መስዋዕትነት ውጤት ነው።

ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

በአማራ ክልል የተገኘው ሠላም የሠራዊታችን ክቡር መስዋዕትነት ውጤት ነው ሲሉ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ተናገሩ።

ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ በሰሜን ጎንደር ዞን ከደባርቅ ወረዳ አስተዳደር የፀጥታ አካላት ጋር በዞኑ አሁናዊ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ውይይት ባደረጉበት ወቅት  ሠራዊታችን በማይበገረው የዓላማ ፅናቱ እንዲሁም  ጀግንነቱ  ክልሉን ከፅንፈኛው መፈንጪያነት ወደ አስተማማኝ ሠላምና ልማት እንዲመለስ አድርጓል ብለዋል።

ፅንፈኛው ኃይል ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስና ስልጣንን ኢ-ህገ መንግስታዊ በሆነ መንገድ ለመያዝ በታሪካዊ ጠላቶቻችን እየተነዳ ያደረገው የቀቢፀ ተስፋ ሙከራ ከባድ ዋጋ አስከፍሎታልም ብለዋል ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ።

እኛ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስና ስልጣን በአቋራጭ ለመያዝ የሚመጡ ኃይሎችን ስርዓት እናስይዛለን እያደርግን ያለንውም ይሄንኑ ነው ያሉት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ዋጋ የከፈልንበትን ሠላም ማፅናትና በቁርጠኝነት መስራት ከአስተዳደር  እንዲሁም ከፀጥታ አካለቱ የሚጠበቅ ቁልፍ ተግባር ስለመሆኑም አሳስበዋል።

በክልሉ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ማስቀጠልና የአካባቢውን ሠላም መጠበቅ  እንዲሁም ከአካባቢው ማህበረሰብ፣ ከሀገር ሽማግሌዎችና የሐይማኖት አባቶች ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባም አቅጣጫ አመላክተዋል።

የዞኑ የፀጥታ ኃላፊዎችም  ሚሊሺያ፣ ሠላም አስከባሪውና መደበኛ ፖሊስ ራሱን አደራጅቶ የክልሉን ብሎም የዞኑን ሠላም ለመጠበቅና ለማፅናት በትኩረት እየተሰራ ስመሆኑንም ተናግረዋል።

የአካባቢው ማህበረሰብ የፅንፈኛውን አድራጎት ተረድቷልም ተገንዝቧልም ያሉት የውይይቱ ተሳታፊዎች አሁንም ሠላሙን ለማፅናት ራሱን አደራጅቶ ስለ ሠላም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነው ብለዋል። ዘጋቢ አንዷለም ከፍያለው ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ

http://localhost/defensenew

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

https://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

as1
ኢትዮጵያ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካዊያን ለመፍታት በቁርጠኝነት እየሠራች መሆኗን የመከላከያ ሚኒስትሯ ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ገለፁ።
as
ኢትዮጵያ እና ኮንጎ ሪፐብሊክ (ብራዛቢል ) በወታደራዊ መስኮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
s6
በአምባሳደር ጄነራል ባጫ ደበሌ የተፃፈው ''የፀረ-ሽምቅ ውጊያ ጥበብ'' መፅሐፍ ተመረቀ።
mf
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች አካል መሆን እንዳለባት የፈረንሣይ የምድር ኃይል አዛዥ ጄነራል ፒየር ሺል ገለፁ።
ay3
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ከኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።
Y
ፈረንሣይ ከኢትዮጵያ ጋር በወታደራዊ መስክ የበለጠ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን የፈረንሣይ ምድር ጦር አዛዥ ጄኔራል ፒየር ሺል ገለፁ።

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ