የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 16 ቀን 2017 ዓ.ም
የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምን ለአራት ቀናት ተመልክቷል።
የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጀኔራል አብዱራህማን እስማኤል የዘንድሮው የእቅድ አፈፃፀም ውይይት ከወትሮው ለየት የሚያደርገው ሀገራችን ባከናወነቻቸው ዘርፈ ብዙ የሪፎርም ተግባራት በዓለምአቀፍ እና አህጉራዊ መድረኮች ያላት ተቀባይነት እና ተደማጭነቷ እያደገ በመምጣቷ በተቋማችንም በወታደራዊ ዘርፉ ከተለያዩ ሀገራት ጋር የሚደረጉ የወታደራዊ ጉዳዮች ትብብር እያደገ ሀገራት ከእኛ ጋር በትብብር ለመስራት የተነሱበት ወቅት መሆኑ ነው ብለዋል፡፡
በዋና መምሪያው ስር የሚገኙ የመምሪያ እና የክፍል ሃላፊዎች በተሰጣቸው ተልዕኮ እና በእቅዱ መሰረት አፈፃፀማቸውን በማስመልከት ባቀረቧቸው ሪፖርቶች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ እንደተቀመጠው በበጀት ዓመቱ ዋና መምሪያው የሠራዊቱን ሁለንተናዊ ዝግጁነት በማረጋገጥ ረገድ በሁሉም ዘርፍ የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት ሰፊ ስራ ተሠርቷል።
የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ሃላፊ ሌተናል ጀኔራል አብዱራህማን እስማኤል በመርሐ ግብሩ ማጠቃለያ ላይ አፈፃፀማችን የተቋማችንን ፈጣን ለዉጥ ታሳቢ በማድረግ፣ ከፍተኛ ወጪ የሚያስወጡ ትጥቆች በውስጥ አቅም በማዘጋጀት ወጪን በመቀነስ፣ አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን እና ወጤታማነትን በማሳደግ ሁለንተናዊ ዝግጁነታችንን ያረጋገጥንበት የአፈፃፀም ብቃት ከፍ ብሎ የታየበትና አዳዲስ የስራ ባህል የተላመድንበት አመት ነው ብለዋል።
የሰራዊቱን የዕለት ተዕለት ቀለብ፤ አልባሳት፣ ትጥቅ እንዲሁም ሞብሊቲን በማረጋገጥ የውጊያ ድጋፍ አገልግሎት አሰጣጡን እያሳለጠ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በልማቱ ዘርፍም በተቋማችን እንዲተገበሩ የታቀዱ የልማት ስራዎች ውስጥ የማዕከሎች የግንባታ ስራ በማጠናቀቅ እና በማልማት አመራሩና ሙያተኛው የተሰጡትን ተልዕኮዎች በአግባቡ አሳክቶ ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲያደርስ፤ የሥራ ተነሳሽነቱ ይበልጥ እንዲጨምር መደረጉንም አንስተዋል።
በአዳዲስ ሀሳቦች ችግር ፈቺ ወጪ ቆጣቢ አሰራሮች ላይ አተኩሮ እንዲሰራ ማዕከላቱን ውብ፣ ፅዱ እና ለስራ የተመቹ የማድረግ ስራ መሠራቱን ገልፀዋል።
ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን ኢስማኤል በተቋማችን የተጀመረውን የሪፎርም ትግበራ የሚያሳኩ፣ የአመራሩንና የሙያተኛውን የመፈፀም አቅም የሚያሳድጉ የሰነ-ልቦና ግንባታዎች፣ ስልጠናዎች በተከታታይ በመከናወናቸው አሁን ላይ በሙያዊ ስነ-ምግባር የታነፀ ወታደራዊ ባህል እና ጨዋነትን ያከበረ የተቋቋመበትን ተልእኮ እና የሚሰጠውን ግዳጅ ታሳቢ ያደረገ አባላት መፍጠር መቻሉን አንስተዋል።
በሰላምም ሆነ በውጊያ የሚኖር ተልዕኮን በማገናዘብ፣ ሃብትን በአግባቡ የሚያስተዳድር፣ ቀልጣፋ፣ የማይቋረጥ፣ ወጪ ቆጣቢና ውጤታማ የውጊያ አገልግሎት ድጋፍ በተፈለገው ጊዜና ቦታ በፍጥነትና በጥራት መስራት የሚያስችል የሎጀስቲክስ አቅም የተፈጠረ መሆኑ በውይይቱ ተገልፃል፡፡ ዘገባው የወርቅነህ ተስፋው ነው
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
http://localhost/defensenew/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.co





