ክብርት ኢንጅነር አይሻ መሃመድ እና በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲስ ላሜክ የመከላከያ ሠላም ማስከበር ማዕከልን ጎበኙ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 28 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ኢንጅነር አይሻ መሃመድ እና በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲስ ላሜክ በመከላከያ ሠላም ማስከበር ማዕከል የአለም አቀፍ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት አሁናዊ የስራ እንቅስቃሴን ተመልክተዋል።

ጉብኝቱ በፈረንሳይ መንግስት የሚሰጡ አጫጭር ስልጠናዎች በሠላም ማስከበር ተሳትፎ ላይ ያላቸውን አዎንታዊ ገፅታ ለመመልከት እና ቀጣይ በሚሰጡ ስልጠናዎች በጋራ ለመስራትና ድጋፍ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲስ ላሜክ  ጉብኝቱ የሁለቱን ሀገራት ሕዝብና መንግስት የረጅም ጊዜ ወዳጅነት ለማጠናከር እንደሚረዳ ገልፀው ቀጣይ በሚሰጡ ስልጠናዎች ከማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
      
የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሃመድ በበኩላቸው የፈረንሳይ መንግስት የሚሠጠው አጫጭር ስልጠና አለም አቀፍ የሠላም ማስከበር ግዳጃችንን በተሻለ መንገድ እንድንፈፅም እገዛ የሚያደርግ ነውና ለቀጣይም የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡

የመከላከያ ሠላም ማስከበር ማዕከል አዛዥ ሜጀር ጄኔራል አዳምነሀ መንግስቴ የፈረንሳይ መንግስት እያደረገ ሥላለው ድጋፍ በመከላከያ ሠላም ማስከበር ማዕከል ስም አመሥግነዋል፡፡

ዘጋቢ ተፈራ ጥላዬ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
http://localhost/defensenew/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av

ወቅታዊ አጀንዳ

as1
ኢትዮጵያ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካዊያን ለመፍታት በቁርጠኝነት እየሠራች መሆኗን የመከላከያ ሚኒስትሯ ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ገለፁ።
as
ኢትዮጵያ እና ኮንጎ ሪፐብሊክ (ብራዛቢል ) በወታደራዊ መስኮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
s6
በአምባሳደር ጄነራል ባጫ ደበሌ የተፃፈው ''የፀረ-ሽምቅ ውጊያ ጥበብ'' መፅሐፍ ተመረቀ።
mf
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች አካል መሆን እንዳለባት የፈረንሣይ የምድር ኃይል አዛዥ ጄነራል ፒየር ሺል ገለፁ።
ay3
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ከኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።
Y
ፈረንሣይ ከኢትዮጵያ ጋር በወታደራዊ መስክ የበለጠ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን የፈረንሣይ ምድር ጦር አዛዥ ጄኔራል ፒየር ሺል ገለፁ።

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ