ዕዙ ለሁለት ወራት ያሰለጠናቸዉን አመራሮች አስመረቀ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም

የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ለሁለት ወራት ያሰለጠናቸዉን የዕዙ እና የሪፐፕሊካን ጥበቃ ሃይል የሻምበል እና የሻለቃ አመራሮች ያስመረቀ ሲሆን በምረቃ ስነ-ስርዓቱም የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጀነራል ሹማ አብደታ በክብር እንግድነት ተገኝተዉ ለአመራሮቹ መልዕክትና የስራ መመሪያ አሥተላልፈዋል፡፡

አመራሮቹ ከአሁን በፊትም ሲመሩ የመጡ እና ግዳጃቸዉን በብቃት መፈፀም የቻሉ መሆናቸዉን ጠቅሰዉ አሁን ደግሞ በስልጠና ያገኙትን አቅም እና እዉቀት ደምረዉ ዉጤታማ ስራ ለመስራት የሚያስችል አቅም መፍጠራቸዉን ጠቅሰዋል፡፡

የነበሩትን ጠንካራ ጎኖች በማቀብ እና ክፍተቶችን በመሙላት እንዲሁም ግዳጅን በአጭር ጊዜ መፈፀም የሚያስችል ቁመና በመገንባት በተገቢዉ መንገድ መስራት ይጠበቅባችኋል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ አመራሮች አና የሪፐፕሊካን አመራሮች በጋራ መሰልጠን አንዱ ለአንዱ ጋሻ እና ደጀን በመሆን ግዳጅን ለመፈፀም እንደሚያስችል የጠቀሱት ሌተናል ጀነራል ሹማ አብደታ ቀይ ቦኔት ሁኔታ ቀያሪ እና ዲስፕሊን መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

የሰልጣኞችን የቆይታ ጊዜ በማስመልከት ለክብር እንግዳዉ የስላጠና ሪፖርት ያቀረቡት የአመራር ትምህርት ቤት አዛዡ ሌተናል ኮሎኔል ሰማሃኝ ሃይሉ የተሰጠዉ ትምህርት የአመራር ትምህርት መሆኑን በመጥቀስ ስልጠናውም የነበረዉን ክፍተት እንዲሞላ እና የመሪነት ሚናዉን ለማሳደግ በሚያስችል መልኩ እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡

ተመራቂ አመራሮቹም የወሰዱት ስልጠና ጊዜዉን ያገናዘበ እና ጥሩ አቅም እና ግንዛቤ የጨበጡበት እንዲሁም በቀጣይ ግዳጅን በአጭር ጊዜ በላቀ ውጤት መፈፀም የሚያስችል የንድፈ ሀሳብ እና የተግባር ትምህርት እንደነበረ  በስልጠና ላይ የቆዩት ሻለቃ ሃብቱ ገብረኪዳን እና ሻለቃ ሽባበዉ ፈጫሳ ገልፀዋል፡፡

ዘጋቢ ምህረት ስመኝ
ፎቶግራፍ አብዱራህማን ሀሰን

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
http://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

p
የኢትዮጵያ ሠላም አሥከባሪ በማንኛውም አይነት ፈታኝ ሁኔታ ሳይረታ ተልዕኮውን እየተወጣ ነው፡፡   ብርጋዴር ጄኔራል ሺሺር ባራድዋጅ
m
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ከሪፖርታጅ ፕሮፐርቲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ስምምነት ተፈራረመ።
j
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ያስመዘገበውን አስደናቂ ለውጥ ይበልጥ ማጠናከር ይገባል፦    ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።