የመቻል ጤና እግር ኳስ ቡድን የአንደኛ ዲቪዚዮን የዋንጫ አሸናፊ ሆነ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 30 ቀን 2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት አዘጋጅነት ከጥር 04 ቀን እስከ ግንቦት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ሲካሄድ የነበረው የአንደኛ ዲቪዚዮን በመቻል ሁለተኛ ዲቪዚዮን በአቃቂ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ  አሸናፊነት ተጠናቋል።

በመዝጊያ ፕሮግራም ላይ በመገኘት ለአሸናፊ ቡድኖች የዋንጫ እና ሜዳሊያ የሠጡት የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ፕሬዘዳንት የእሳት እና ድንገተኛ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አህመድ መሃመድ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ናቸው።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው የፍፃሜ ጨዋታ መቻል ጤና እግር ኳስ ቡድን የሚኒሊክ ሆስፒታል አቻውን 3ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል። መቻል ባለድል የሆነበትን ሶስቱንም ጎሎች አስር አለቃ አንተነህ ጌታቸው ከመረብ አሳርፏል።

የውድድሩ ኮከብ አሰልጣኝ የመቻሉ ሻምበል ወንደወሰን በየነ ሲሆን ፣ 10 ጎሎችን በማስቆጠር መቶ አለቃ ደረጄ ግዛው ኮከብ ጎል አስቆጣሪ ፣ አምሳ አለቃ ግርማ ገቢሳ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ሶስቱም ከመቻል አሸናፊ በመሆን ሽልማታቸውን ከክብር እንግዶች ተረክበዋል ።

የመቻል ጤና እግር ኳስ ቡድን በሃልም ኢንተርናሽናል እና በአንበሳ ስፖርት ትጥቅ አምራች ስፖንሰር አድራጊነት በተደረገው የእግር ኳስ ውድድር በይቻላል አንድ ለዜሮ ተሸንፈው ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ የብር ሜዳልያ ተሸላሚ ሆኗል።

ወድድሩ የሚቀጥል ሲሆን በ18ኛው የመንግስት መስሪያ ቤቶች የእግር ኳስ ውድድር መከላከያ ሠራዊት እግር ኳስ ቡድን ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር ሰኞ ሰኔ 01 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም የፍፃሜ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በተያያዘ ዜና የመቻል ከ17 ዓመት በታች የሮሃ አቻውን 8ለ0 በሆን ሰፊ ውጤት አሸንፏል።

በገረመው ጨሬ

ወቅታዊ አጀንዳ

p
የኢትዮጵያ ሠላም አሥከባሪ በማንኛውም አይነት ፈታኝ ሁኔታ ሳይረታ ተልዕኮውን እየተወጣ ነው፡፡   ብርጋዴር ጄኔራል ሺሺር ባራድዋጅ
m
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ከሪፖርታጅ ፕሮፐርቲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ስምምነት ተፈራረመ።
j
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ያስመዘገበውን አስደናቂ ለውጥ ይበልጥ ማጠናከር ይገባል፦    ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።