የሚሰጠውን ግዳጅ በድል መወጣት የሚችል አዋጊና ተዋጊ ሠራዊት ተገንብቷል።

   የኮር እና የክፍለጦር አመራሮች

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም

የሚሰጠውን ማንኛውንም ውስብስብና ፈተኝ ግዳጆች በድል መወጣት የሚችል ሠራዊት ተገንብቷል ሲሉ የስድስተኛ ዕዝ ኮር አዛዥ ብርጋዲየር ጄነራል ሃብታሙ ምህረቴ ተናገሩ።

የዕዙ የሠራዊት አባላት በውስብስብ ሁኔታዎች ሳይበገር ህዝብና መንግስት የሰጡትን ተልዕኮዎች በጀግንነት፣ በውጤታማነትና በድል እየተወጣ የህብረተሰቡን ሰላም እያረጋገጠ ይገኛል ያሉት አመራሮቹ በተደረጉ የስምሪት ስራዎች የላቀ ውጤት ማስመዝገቡንና አስደናቂ ገድሎች መፈፀማቸውን አውስተዋል።

ሠራዊቱ በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች ከሚገኙ ነዋሪዎች ጋር በተደረጉ ሰፋፊና ተከታታይ ህዝባዊ መድረኮች አሸባሪው የሸኔ ቡድን እና ፅንፈኛው  ፈጥረውት የነበረውን ችግር ማጥራት የተቻለ መሆኑን ተናግረዋል።

የዕዙ አባላት ሞራላዊና ስነ-ልቦናዊ ዝግጁነት የመገንባት ፣ የአሃዱዎችን ግዳጅ የመፈፀም እና የማድረግ አቅሞች  የማሳደግ ፣በየደረጃዉ የሚገኙ አመራሮችን ዙሪያ-መለስ የመምራት አቅም የማጎልበት እንዲሁም የተለያዩ ሙያተኞችን በየተመደቡበት ዘርፍ ሙያዊ ብቃታቸዉን የማሳደግ ስራ በስፋት መሠራቱን ገልፀዋል።

ስልጠናዎችም የዘመናዊ ሠራዊት ግንባታ ሂደቱን መነሻ በማድረግ ከውጊያ ፅንሰ-ሃሳብ ጀምሮ እስከ አሃድ መምራትና ለዉጊያ ማዘጋጀት እንዲሁም ግዳጅ ተኮር የስልጠና ስምሪት በማከናዎን ተደማሪ የማድረግ አቅሞችን ለመፍጠር በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል።

ዘጋቢ አዲሱ አራጋው

ፎቶግራፍ ሌሊሴ አራራሜ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ

http://localhost/defensenew

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

https://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ
SS1
ከተጣሉበት በማንሳት በራስ አቅም ተሻሽለው ወደ ሀይል የገቡት ትጥቆች የተቋሙን የውጊያ አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራሉ።     ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
SSS
የሜጀር ጀኔራል ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለተቋምና ለሀገር የሚሠጠውን ጥቅም ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።
ASH
የውስጥ አቅሞችን አሟጦ በመጠቀም ለተቋማዊና ሀገራዊ ጥቅም ማዋል ይገባል።  ክብርት ኢንጅነር አይሻ መሀመድ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ