የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል ስኬታማ የግዳጅ አፈፃፀም ማስመዝገቡ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሰኔ 28 ቀን 2017 ዓ.ም

የሪፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል የፀረ-ሰላም ሀይሎችን እንቅስቃሴ በመግታት መስዋዕትነት ከፍሎ ሀገርን ከመፍረስ የታደገ ክፍል ነው ሲሉ ጀኔራል ጌታቸው ጉዲና ተናገሩ።

ክፍሉ በውጊያ ውስጥ ሁኔታን የሚቀይር ለሌሎች ክፍሎች የውጊያ እንቅስቃሴን የሚያመቻች ጀግና እና አርአያ የሆነ ክፍል ነው ብለዋል።

የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል በአጭር ጊዜ በመደራጀት በርካታ የሀገር መሪዎችን እና ዲፕሎማቶችን ደህንነት በተሟላ መንገድ የመጠበቅ ተልዕኮውን በተሳካ ሁኔታ መፈፀሙን ገልፀዋል።

ጀኔራል ጌታቸው የሪፐብሊኩ ጥበቃ ሃይል አባላት ዘንድሮ የተመዘገበውን ውጤት ቀጣይም አስጠብቃችሁ በተሻለ ውጤት እንደምታስቀጥሉ እምነቴ የፀና ነው ብለዋል።

በአመቱ ከጓድ መሪ ጀምሮ እስከ ሻለቃ አመራር ድረስ የተሰጠው ስልጠና እንዲሁም በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ የተሰጡ የተለያዩ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ክፍሉ የተሻለ የማድረግ አቅም እንዲኖረው ያሥቻለ መሆኑን ገልፀዋል።

የጥበቃ ሃይሉ የተለያዩ ሀገር ዲፕሎማቶችን በክብር በመቀበልና በመሸኘት የሀገርን ገፅታ በመገንባትና መሪዎች ደህንነታቸው ተጠብቆ የተለያዩ አለማቀፋዊ እና አህጉራዊ ስብሰባዎች በስኬት እንዲጠናቀቁ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በአስተማማኝ ሁኔታ የቆመለትን አላማ እየፈፀመ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በመዝገቡ ያረጋል

ወቅታዊ አጀንዳ

as1
ኢትዮጵያ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካዊያን ለመፍታት በቁርጠኝነት እየሠራች መሆኗን የመከላከያ ሚኒስትሯ ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ገለፁ።
as
ኢትዮጵያ እና ኮንጎ ሪፐብሊክ (ብራዛቢል ) በወታደራዊ መስኮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
s6
በአምባሳደር ጄነራል ባጫ ደበሌ የተፃፈው ''የፀረ-ሽምቅ ውጊያ ጥበብ'' መፅሐፍ ተመረቀ።
mf
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች አካል መሆን እንዳለባት የፈረንሣይ የምድር ኃይል አዛዥ ጄነራል ፒየር ሺል ገለፁ።
ay3
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ከኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።
Y
ፈረንሣይ ከኢትዮጵያ ጋር በወታደራዊ መስክ የበለጠ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን የፈረንሣይ ምድር ጦር አዛዥ ጄኔራል ፒየር ሺል ገለፁ።

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ