የውጭ ጠላቶቻችን ኢትዮጵያን አቅም የሌላትና ደካማ ሀገር ለማድረግ ከመስራት አይቆጠቡም   ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሃምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም

የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ተገኝተው ከዕዙ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በየአቅጣጫው ነፍጥ እያነሱ ህዝባችንን ሰላም የሚነሱና ልማት የሚያደናቅፉ የሀገር ውስጥ ፅንፈኞች፣ የተፈጥሮ ሀብታችንን እንዳናለማና ጠንካራ ኢትዮጵያ እንዳትኖር የሚፈልጉ የውጭ ጠላቶቻችን ተላላኪና ጉዳይ አስፈፃሚ ባንዳ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ በየጊዜው በሚፈጠሩ ሀገር ወዳድ አርበኞቿ ፀንታ የቆመች ናት ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ፣ የአርበኞቻችንን ያክል ቁጥር ባይኖራቸውም የውስጥ ባንዳም ያልተለያት ሀገርም ናት ብለዋል።

አሁንም አገርን ለመበታተን እየተፍጨረጨሩ ያሉ የውጭ ተላላኪና ጉዳይ አስፈፃሚ ባንዳዎችን በመደምሰስ የሀገርን አንድነት ያስቀጠለው ሠራዊታችን የዚህ ዘመን አርበኛ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የውጭ ጠላቶቻችን ምንጊዜም የማይተኙልን በመሆናቸው፣ ሠራዊታችንን ጠንካራ፣ አስተማማኝና ግዳጁን በብቃት መፈፀም የሚችል አድርገን ገንብተነዋል ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በዚህ ሠራዊት ሀገርም እኔም እንኮራለን፣ እናንተም ክብር ይገባችኋል ብለዋል።

ወቅታዊ አጀንዳ

p
የኢትዮጵያ ሠላም አሥከባሪ በማንኛውም አይነት ፈታኝ ሁኔታ ሳይረታ ተልዕኮውን እየተወጣ ነው፡፡   ብርጋዴር ጄኔራል ሺሺር ባራድዋጅ
m
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ከሪፖርታጅ ፕሮፐርቲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ስምምነት ተፈራረመ።
j
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ያስመዘገበውን አስደናቂ ለውጥ ይበልጥ ማጠናከር ይገባል፦    ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።