ጦርነትን ለማሸነፍ የስነ-ልቦና ዝግጁነት ወሳኝ መሆኑን ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ ተናገሩ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም

ጦርነትን ለማሸነፍ የስነ-ልቦና ዝግጁነት ወሳኝ ነው ሲሉ የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ ተናገሩ።

ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ በሰሜን ምዕራብ ዕዝ  ማሰልጠኛ ማዕከል ተገኝተው በስልጠና ላይ ለሚገኙ የሬጅመንትና ሻምበል አመራሮች በሠራዊት የስነ-ልቦና ግንባታ  ዙሪያ ትምህርት በሰጡበት ዕለት የተቋማችንን የፕሮፌሽናል ሠራዊት ግንባታ ስኬታማ ለማድረግ ደስተኛና በራሱ የሚተማመን፤ ስነ-ልቦናና አካላዊ ብቃቱ የተረጋገጠ ሁለንተናዊ አቅም ያለው አመራርና ሠራዊት ማዘጋጀት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

ሌተናል ጄንራል ጥጋቡ ይልማ የሠራዊቱን ስነ-ልቦና ለማረጋገጥ በስልጠናና በዕውቀት ክህሎትን በማዳበር ከዘመኑ ጋር የሚዘመን በጠንካራ ስነ-ልቦና የምንመራው የጦር ክፍል ማሰልጠን፣መገንባትና ማብቃት  ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የምንመራው ሠራዊት አቅሙ እንዲጎለበትና የሚሰጠውን ግዳጅ በድል እንዲወጣ አመራሩ ተከታታይነት ያለው የስነ-ልቦና ግንባታ ስራዎችን መስራት  ይጠበቅበታል ብለዋል።

የመከላከያ ጤና ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ  ፅንፈኛውን ኃይል በመደምሰስ በመስዋዕትነታችን ያረጋገጥነውን ሠላም የበለጠ ለማፅናት አቅማችንን ማጎልበትና ተልዕኳችንን በላቀ ብቃት ለመወጣት የበለጠ መዘጋጀት እንደሚገባም አሳስበዋል።

ዘጋቢ ይሁን አሻግሬ
ፎቶግራፍ እያሱ ጃርሶ 

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

as1
ኢትዮጵያ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካዊያን ለመፍታት በቁርጠኝነት እየሠራች መሆኗን የመከላከያ ሚኒስትሯ ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ገለፁ።
as
ኢትዮጵያ እና ኮንጎ ሪፐብሊክ (ብራዛቢል ) በወታደራዊ መስኮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
s6
በአምባሳደር ጄነራል ባጫ ደበሌ የተፃፈው ''የፀረ-ሽምቅ ውጊያ ጥበብ'' መፅሐፍ ተመረቀ።
mf
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች አካል መሆን እንዳለባት የፈረንሣይ የምድር ኃይል አዛዥ ጄነራል ፒየር ሺል ገለፁ።
ay3
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ከኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።
Y
ፈረንሣይ ከኢትዮጵያ ጋር በወታደራዊ መስክ የበለጠ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን የፈረንሣይ ምድር ጦር አዛዥ ጄኔራል ፒየር ሺል ገለፁ።

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ