ራሱን የነዘመነ ቡድን ብሎ የሚጠራው ፅንፈኛ ለሰሜን ሜጫ አስተዳደር እጅ ሰጠ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

መንግስት ያስተላለፈውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ከነ ሙሉ ትጥቃቸው እጃቸውን የሰጡት 12 በሰሜን ጎጃም  ጫካ ገብተው የነበሩ አመራሮች ናቸው።

እጅ በሰጠው ቡድን ስር በራሱ አደረጃጀት እራሱን የኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ ብሎ ከሚጠራው መካከል

1. ሻምበል መንግስቱ ድልነሳ አለም –  ሻለቃ አዛዥ

2. መቶ አለቃ ምስጋናው ሽታ ገረመው – ሻለቃ ዘመቻ ሀላፊ

3. ዶክተር አንለይ አሰፋ ዘላለም – በአቸፈር ቀጠና አቤ ጎበኛ ብርጌድ አስተዳደር እና ጸጥታ ሀላፊ እና ሌሎች ስምንት አመራሮች እና አባላቱ መንግሰት የሰጣቸውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው እጅ ሰጥተዋል።

በሰላም እጅ ሲሰጡ የሰሜን ጎጃም ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ሀላፊ አቶ ገብረስላሴ ታዘብ፣ የምስራቅ ዕዝ አንድ ኮር አመራሮች ፣ የመርዓዊ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ብርሃኑ አበረ፣ የመርዓዊ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌታነህ መልኬ ተገኝተዋል።

እጅ ከሰጡት መሐል አንዳንዶቹ እንደተናገሩት ፣ እስካሁን የሄድንበት የተሳሳተ መንገድ በመሆኑ እኛም፣ ቤተሰቦቻችንም እና መላ ህዝባችንም ብዙ ዋጋ ከፍለናል፤ ብዙ ወንደሞቻችን እና እህቶቻችን አጥተናል፤ ተጨማሪ ህይወት መጥፋት የለበትም፤ ነገ ድርድር ቢደረግ የማናገኛቸውን ወጣቶች ማጣት የለብንም ብለን የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለን የህዝባችንን መከራ ለማቆም ወስነን እጅ ሰጥተናል ብለዋል።

አሁንም በተሳሳተ መንገድ ላይ ያሉ ወንድሞቻችን የእኛን ፈለግ ተከትለው መንግስት የዘረጋው የሰላም እጅ ሳይታጠፍ ህይወታቸውን ለቤተሰቦቻቸው እንዲያቆዩ ወንድማዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ብለዋል።

በተያያዘ ዜና በአዴት ዙሪያ በዴንሳባታና በአጊታ ቀበሌ የተሰማራው በምስራቅ ዕዝ ስር የሚገኝ አንድ ሬጅመንት በፅንፈኛው ቡድን ላይ በወሰደዉ እርምጃ አስር የጠላት ሀይል ሲደመስስ አንድ መትረየሰ ማርኳል፡፡

የዕዙ የሠራዊት አባላት በተሰማሩባቸዉ የግዳጅ ቀጠናዎች የሰላምን አማራጭ ባልተቀበሉ የፅንፈኛው ቡድን ላይ እግር በእግር እየተከታሉ የመደምሰሱን ተግባር አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡

ሰሞኑን በአዴት ዙሪያ በዴንሳባታና በአጊታ ቀበሌ ከጠላት ጋር የተደረገዉን ኦፕሬሽን አስመልክተው የአንድ ሬጅመንት አዛዥ ሻለቃ ባሻ ፈንታሁን አሰፋ እንደተናገሩት፣ በነበረን ስምሪት ጠላትን ከገባበት ገብቶ በማሳደድ ጠንካራ ምት አሳርፈንበታል፤ በዚህም ዘመቻ አስር የጠላት ሀይል በመደምሰስ 12 በማቁሰል ፣ አንድ ፒ ኬ ኤም/መትረየስ ፣ አንድ ባለ 100 የመትረየስ ሸንሸል፣ ሁለት ክላሽ ፣ ሁለት ካዝና ፣ ሰባት ቃታ መሳሪያ ፣ አንድ የስናይፐር መነፅር እና 187 ተተኳሽ ጥይት ማርከናል ብለዋል፡፡

በተሰለፍንበት የግዳጅ ቀጠና የአካባቢዉ ህብረተሰብ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ እና ወደ  መሰረተ ልማት የበለጠ ትኩረቱን አድርጎ እንዲሰራ የምናደርገዉን የጠላት ሀይል ለይቶ የመደምሰስ ግዳጃችንን ከአካባቢዉ ህብረተሰብና የፀጥታ አካላት ጋር አቀናጅተን እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ ታደሰ ይሴ

ፎቶግራፍ ከሬጅመንት

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ

http://localhost/defensenew

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
http://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።