የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ሚያዚያ 07 ቀን 2017 ዓ.ም
የኢፌዴሪ መከለከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በኢትዮጵያ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት እያደረገ ለሚገኘውና በቤላሩስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማክሲም ሪዚሄንኮቭ የተመራውን ከፍተኛ ልዑክ በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
ኢንጂነር አይሻ ከሌሎች የመከላከያ አመራሮች ጋር በመሆን ለልዑካን ቡድኑ አቀባባል ያደረጉላቸው ሲሆን በተለይም በሁለቱ አገራት መካካል በወታደራዊና ፀጥታ ዘርፎች ትብብርን ለማስፋት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
ሚኒስትሯ በዚሁ ወቅት ሁለቱ አገራት የጋራ እሴት፣ ታሪክና የባህል መመሳሰል ያላቸው በመሆኑ ይህንን እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማሳደግ ኢትዮጵያ ፍላጎት እንዳላት ገልፀውላቸዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በበኩላቸው ሁለቱ አገራት በወታደራዊ ስልጠና፣ የመከላከያ ቴክኖሎጂ ልውውጥና በመሳሰሉ መስኮች ትብብርን ማሳደግ አስፈላጊ በመሆኑ ለዚሁ እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በተጨማሪም በኢትዮጵያ እያደረጉት ባለው ይፋዊ የስራ ጉብኝትና ውይይት በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድንና በባህል ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችሉ ዕድሎች መኖራቸውንና እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶችም ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን መገንዘባቸውን ጠቅሰው ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል የበለጠ ጠንካራ አጋርነት እንዲኖር መንገድ የሚከፍት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ዘገባው የሚኒስቴሩ ፅህፈት ቤት ነው።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
