የመከላከያ ሚኒስቴር ባለፉት ዘጠኝ ወራቶች አበረታችና ውጤታማ ተግባራት አከናውኗል- ኢንጂነር አይሻ መሀመድ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈፃፀም ውይይት አድርጓል። የሥራ አፈፃፀም ሪፖርቱን ያቀረቡት የሚኒስቴሩ እቅድ እና ሪፖርት ዝግጅት ክትትል ዳይሬክተር ኮሎኔል ፈይሳ ታደሰ በአንዳንድ ክፍሎች ላይ በስራ ሂደት እንቅስቃሴ ውስጥ ካጋጠሙ ችግሮች እና ከታዩ ክፍተቶች ውጭ ሁሉም ፈፃሚ አካላት ስራቸውን በትጋት በመፈፀማቸው አበረታች ውጤት መገኘቱን ተናግረዋል።

ሠራዊቱን ከአዳዲስ ቴክኖሎጅ ጋር በማዋሀድ በአስተማማኝ መልኩ ሠላምን እንዲጠብቅ በማድረግ በኩል ከፍተኛ ተግባራት መከናወኑን አንስተዋል። የኢንዱስትሪዎችን አቅም በማሳደግ፣ ወታደራዊ ዲፕሎማሲውን ከፍ በማድረግ፣ የሰው ሀብት አቅምን በማደራጀት እና በማዘመን፣ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ትምህርታዊ፣ ሙያዊ እና ወታደራዊ ስልጠናዎች የመስጠት ሥራዎች መተግበራቸውም ተመላክቷል።

የተቋሙን ገፅታ መገንባት፣ የሙስና ወንጀሎችን መከላከል፣  ለደንበኞች ፍትሀዊ የዳኝነት አገልግሎት መስጠት፣ የስርዓተ- ፆታን ግንዛቤ ማሳደግ በአጠቃላይ ተቋሙ በተሰማራባቸው የስራ ዘርፎች  አበረታች ውጤት መገኘቱ በውይይቱ ተገልጿል።

ከተወያዮች የተነሱ ሀሳቦችን እና ጥያቄዎችን መነሻ በማድረግ ማብራሪያ የሰጡት የመከላከያ ሚኒስትሯ  ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ባለፉት ዘጠኝ ወራቶች የተሠራው አጠቃላይ ሥራ ውጤታማና የሚበረታታ መሆኑን ገልፀው በአራተኛው ሩብ ዓመት ይበልጥ የተሻለ የእቅድ አፈፃፀም ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉም ራሱን ዝግጁ ማድረግ እና መታተር እንደሚገባው አመላክተዋል።

ፈፃሚ አካላት የተቋሙን ታላላቅ ግቦች መሰረት ያደረገ የእቅድ አፈፃፀም ውጤት ሊኖራቸው እንደሚገባ

አሳስበው መከላከያ ታላቅ አቅም ያለው አንጋፋ ተቋም በመሆኑ ሙሉ አቅሙን ተጠቅሞ ወደ ውጤት ለመቀየር ከዚህ በላይ ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በብርሃን እንዳየሁ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

http://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።