የሚዲያ ስራችን በሠራዊታችን ተልዕኮና ግዝፈት ልክ መቃኘት ይኖርበታል።ሜጀር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳን

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም

ከመከላከያ ክፍሎች ለተውጣጡ የሥነ ልቦና ግንባታ አመራሮች እና የሚዲያ ሙያተኞች ሲሰጥ የቆየው ሰልጠና ተጠናቋል። በዚሁ የሰልጠና ማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የመከላከያ ሰራዊት ሰነ- ልቦና ግንባታ ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳን ሰራዊታችን የተሠጠውን ሀገራዊና ህዝባዊ አደራ መሠረት አድርጎ የሚያከናውነው ህዝባዊና ሀገራዊ ተልዕኮ በሚገባ አልተነገረለትም ብለዋል።

ይህንን አካሄድ ለማስተካከል የሰራዊቱን ልፋትና ድካም የሚረዱ በእያንዳንዱ ግንባር ድል  ያደረጉ ብዕርና ወረቀታቸውም የጠላትን ሀሰታዊ ፕሮፖጋንዳ ከንቱ የሚያስቀር ጀግና ወታደራዊ ጋዜጠኞች ማፍራት ላይ

ትኩረት በማድረግ እየተሠራ ሥለመሆኑ አንስተዋል።

የሠራዊታችንን ሰነ ልቦና በውጊያም ሆነ ከውጊያ በኃላ ሳይቆራረጥ ተከታታይ በሆነ መልኩ መሰራት ያሥፈልጋል ያሉት ሜጀር ጀኔራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳን ይህ የሚሆነውም የስነ ልቦና ግንባታ የሰራዊታችን የአሸናፊነት ሰንቅ ሰለሆነ ነው ብለዋል።

ሰራዊቱ የሚፈፅመው አኩሪ ተጋድሎ በሚዲያዎቻችን ለህዝባችን እንዲደርስ በተቋሙ ክፍሎች ያሉ የሚዲያ ሙያተኞች ጠንክረው መስራት አለባቸው ያሉት ጀነራል መኮንኑ ስልጠናው የተሰጠውም ከዚህ  አላማ አንፃር መሆኑን ተናግረዋል። በተለይ አሁን ላይ የሚዲያ ነፃነትን በመጥፎ ጎኑ በመጠቀም የሰራዊታችንን ሰምና ዝና ለማጥፋት የሚጥሩ ሃይሎች ያሉ በመሆናቸው የእነዚህን እኩይ ሃይሎች የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ተከታትሎ ማጋለጥ ይገባልም ሲሉ አስገንዝበዋል።

ሜጀር ጀኔራል እንዳልካቸው ወልደ ኪዳን ሰልጣኞች በስልጠናው ወቅት ያገኛችሁትን አቅም በመጠቀም የሰራዊታችንን የዕለት ተዕለት ተልዕኮና እሱን ተከትሎ የሚያስመዘግበውን አኩሪ ተጋድሎ ለሚዲያ ሽፋን በሚሆን መልኩ መሰነድ ፣ መዘገብ ይጠበቅባችኋል ሲሉም አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚን ጨምሮ ለሥልጠናው መሳካት ከፍተኛ አሥተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ሜጄር ጄኔራል እንዳልካቸው ወልደኪዳን ምስጋና አቅርበዋል።

አጠቃላይ የሥልጠናውን ሪፖርት ያቀረቡት የዋና ዳይሬክቶሬቱ የሥልጠና ቡድን መሪ ኮሎኔል መንግስቱ ካታንጋ ስልጠናው በተመደበለት የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በንድፈ ሃሳብና በተግባር ለሥነ ልቦና አመራሮችና ለሚዲያ ሙያተኞች በቀንና በማታ የተሠጠ መሆኑን ጠቁመው ስልጠናው በየክፍላቸው በተግባር ከሚያከናውኗቸው የግንባታ ስራዎች ጋር አያይዘው እንዲመለከቱት መደረጉንም ተናግረዋል፡፡

በማሩ ግርማይ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

http://youtube.com

@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

http://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።