የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ክብሯን ጠብቆ ማሻገር የእኛ ትውልድ ኃላፊነት ነው።

        ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 30 ቀን 2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና ክብሯን ጠብቆ ማሻገር የኛ ትውልድ ኃላፊነት ነው ሲሉ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ተናገሩ።

ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ በአንድ ኮር  በስልጠና ላይ የሚገኙ የመቶና የጓድ አመራሮች የስልጠና ሂደትን በተመለከቱበት ወቅት ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ ክብር መስዋዕትነት ክብሯ ተጠብቆ ዛሬ ላይ ደርሳለች በእኛ ትውልድም የአፍሪካዊያን ኩራትና የነፃነት ተምሳሌት ሆና ትቀጥላለችም ብለዋል።

ኮሩ ፅንፈኛውን ቡድን በመደምሰስ ተልዕኮውን በላቀ ጀግንነት የፈፀመ ነው ያሉት ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ሠራዊቱን በመምራት፣በማስተባበር ራሳችሁም ጭምር ተዋጊ በመሆን አኩሪ ገድል ፈፅሟችኋልም ብለዋል።

ሠራዊቱን በሁለንተናዊ መስክ ለማብቃት የቅርብ አመራሩ ድጋፍና ክትትል ከፍተኛውን ሚና ይጫወታል ያሉት አዛዡ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ብቃት ያለው የመቶና የጓድ አመራር ለጠንካራ ሠራዊት ግንባታ መሠረት ስለመሆኑም ተናግረዋል።

ተቋማችን ለሠራዊት ግንባታ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት ይገኛል ያሉት ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ከዘመኑ ጋር እየዘመነና በቴክኖሎጂ አቅሙ እያደገ በመምጣቱ ለኢትዮጵያ ክብር የሚመጥናት የመከላከያ ኃይል በመገንባት ላይ ስለ መሆኑም ተናግረዋል።

በየደረጃውና በየተመደብንበት የስራ መስክ ውጤታማ ስንሆን የፕሮፌሽናል ሠራዊት ግንባታውን እውን እናደርጋለን ያሉት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ በስልጠና የሚፈጠር ሁለንተናዊ  አቅም ለቀጣይ ተልዕኮ ስኬት የበለጠ የሚያዘጋጅ  መሆኑን በመገንዘብ ለውጤታማነት መትጋት ይጠበቅባችኋል  ሲሉም አሳስበዋል።  

በአንዷለም ከፍያለው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ

http://localhost/defensenew

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

http://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።