ጠንካራና ለቆመለት ዓላማ ፅኑ የሆነ፣ ግዳጁን በድል የሚወጣ ሠራዊት ተፈጥሯል።

ሌተናል ጄኔራል መሃመድ ተሰማ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም

ምስራቅ ዕዝ በገርባሳ ማሰልጠኛ ማዕከል ከሁሉም ኮሮችና ስታፍ ልዩ ልዩ ክፍሎች ለተውጣጡ ሙያተኞችን  እያስለጠነ ይገኛል።

እነዚህ ሰልጣኞች የተለያዩ የሙያ ስልጠና፧ የስነልቦና ፣ የአካል ብቃት እና አሀድን ለውጊያ ማዘጋጀት ፣ የተዘጋጀውን አሀድ መምራት አንዲሁም ሌሎች ክህሎቶችን በመማር ላይ ይገኛሉ።

በማስልጠኛ ማዕከሉ የተገኙት የምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ተሰማ ፣ ጠንካራና ለቆመለት ዓላማ ፅኑ የሆነ፣ ግዳጁን በድል የሚወጣ ሠራዊት መፈጠሩን ጠቅሰው ሠራዊቱ የአገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ፣ የኢትዮጵያን ዳር ድንበርና የህዝብን አንድነት በሀይል ለመናድ የሚሰነዘርን ጥቃት በመመከት የአገራችንን ሰላምና አንድነት የማረጋገጥ ተልዕኮውን በድል እየተወጣ የሚገኝ የድል ሠራዊት ነው ብለዋል።

ሰራዊታችን የአልሸባብን ሴራና ተንኮል በመገንዘብ የምስራቁን ቦርደር አካባቢ እየጠበቀ ያለ መሆኑንና በምስራቅ ሃረርጌና ምዕራብ ሃረርጌ አካባቢ የሸኔን ጥፋት እያመከነ ያለ እንዲሁም በአማራ ክልልም የፅንፈኛውን ሃይል አገር የማፈረስ ተልዕኮ በማክሸፍ ግዳጁን በአስተማማኝ እየተወጣ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ሰአት የሀገራችንን ሰላምና እድገት የማይፈልጉ የውጭና የሀገር ውስጥ ጠላቶች ስላሉብን እየተዋጋን ለትላላቅ ሀገራዊ ግዳጅ መዘጋጀት ስላለብን ስልጠና ላይ የሞትገኙ ሰልጣኝ ሙያተኞች አቅማችሁን ይበልጥ በማጎልበት ተጨማሪ አቅም መፍጠር ይኖርባችኋል ብለዋል።

ሰልጠኞች የተቋሙን ንብረት በጥንቃቄ በመያዝ እና ጠንካራ አሀድ በመገንባት እንዲሁም በግዳጅ ላይ አሃድን በብቃት በመምራት ድል ማስመዝገብ የሚያስችል ክህሎት መኖር አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

ሠራዊቱ የኢትዮጵያን ህብረ ብሔራዊ አንድነቷ ያፀና የበለፀገች አገር፣ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱንና ሃገረ መንግስቱን በመጠበቅ የአገሪቱን ብሔራዊ ክብር ያረጋገጠና መስዋዕትነትን በመክፈል የአገሪቱ የመጨረሻው ምሽግ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የሰለጠነና የተማረ የሰዉ ሃይል በማፍራት ዘመናዊ የሆኑ ትጥቅችን በመታጠቅ ጦርነትን ከሩቁ ማስቀረት የሚችል ሰራዊት እየተገነባ ነው ያሉት ሌተናል ጄኔራል መሃመድ ተሰማ ስልጣኞች ወደ አሃዳችሁ ስትመለሱ በተሰማራችሁበት የስራ ዘርፍ የተሰጣችሁን ተልዕኮ ከፍተኛ በሆነ ውጤት ግዳጃችሁን በጥራት፣ በኃላፊነት፣ ተጠያቂነትና ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ መፈጸም ይገባችኋል ሲሉ አስገንዝበዋል።

ሌተናል ጀኔራል መሐመድ  ተሰማ ሰራዊቱ  ህገ-መንግስቱን በፅናት በመያዝ የተቋማችንን ተልዕኮ ፣ ደንቦች፣ መመሪያዎች፣ ባህሪያትና እሴቶች በመተግበር እና በማስተግበር የአመራር ሚናቸዉን መወጣት እንደሚገባቸው ተናግረዋል ።

ዘጋቢ አወል መሃመድ

ፎቶ ግራፍ ሳምሶን ባህሩ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ

http://localhost/defensenew

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ

http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 

http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ

http://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።