ቴዎድሮስ ኮር በወርቃማ ቀለም የተፃፈ የዘለዓለማዊ ታሪክ ባለቤት ነው”

ሌተናል ጄኔራል መሠለ መሠረት

የምዕራብ ዕዝ ቴዎድሮስ ኮር ሁሌም የተሠጡትን ተልዕኮዎች በአንፀባራቂ ድል የሚፈፅምና በወርቃማ ቀለም የተፃፈ ዘለዓለማዊ ታሪክ ባለቤት መሆኑን የምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሠለ መሠረት ገልፀዋል።

አዛዡ በኮሩ 4ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ቴዎድሮስ ኮር በሠሜኑ ህግ ማስከበር ዘመቻ ከ700 ኪ.ሜ በላይ በእግር ተጉዞ በጠላት ይዞታ ውስጥ በመግባት የጠላትን ቅስም ሠባብሮ ድል መጎናፀፉን አስታውሰዋል።

አሸባሪውን የሸኔ ቡድን የመመንጠር ግዳጅን ተቀብሎ በምዕራብ ኦሮሚያ በመሠማራት በወለጋ አራቱም ዞኖችና በምዕራብ ሸዋ ዞን ግንደ በረትና አቡነ ግንደ በረት ፤ በአዳበርጋ ፤ ሜታ ወልቂጤ እና ሜታ ሮቢ ቀጠናዎች የነበረውን የአሸባሪውን የሸኔ አባላት እና አመራር የደመሠሠ እና የማረከ ፤በርካታ የቡድንና ነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን በእጁ ያስገባ የአናብስት ስብስብ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል መሠለ መሠረት የኮሩ አመራርና አባላት ይህንን ተነግሮ የማያልቅ የድል አድራጊነት እና የአሸናፊነት መንፈሳችሁን አቅባችሁ ሀገር እና ህዝብ እንዲሁም ተቋማችንን የሚያኮራ የላቀ ድል በማስመዝገብ ኢትዮጵያን የማፅናት ተልዕኳችሁን በተጨማሪ ገድሎች አጅባችሁ እንደምትወጡ እምነቴ ፅኑ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ምሬሳ ፊጤ በበኩላቸው ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ከ2014 እስከ 2016 የካቲት ወር መጀመሪያ ያሉት ግዜያት ለሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ሕዝብ መጥፎ ትውስታ እንደነበር አስታውሠው በኦሮማ እና አማራ ህዝቦች ስም በሚነግዱ ፅንፈኛ እና አሸባሪ ቡድኖች ሲደርስበት የነበረውን ግፍ አውስተዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ በንግግራቸው የምዕራብ ዕዝ ቴዎድሮስ ኮር ወደ ዞኑ ከገባ ከየካቲት 2016 ዓ.ም ጀምሮ ከአካቢው ህዝብ እና መስተዳድር ጋር በመቀናጀት የሽብር ቡድኖችን አከርካሪ ሠብሮ ቀጠናው የሠላም አየር እንዲነፍስበት አስችሏል ብለዋል።

አቶ ምሬሳ ፊጤ በመጨረሻም የምዕራብ ዕዝ አመራርና አባላት በተለይም የቴዎድሮስ ኮር ህዝባችንን ከጨለማ ወደ ብርሃን ለማሸጋገር ስትሉ ለከፈላችሁልን ሁለንተናዊ መስዋዕትነት በዞኑ ህዝብና መስተዳድር ስም ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፤ ሁሌም ከጎናችሁ በመሆን ለቀሪ ግዳጆች መሳካት የተለመደ ደጀንነታችን ከምንግዜውም በላይ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

ወቅታዊ አጀንዳ

as1
ኢትዮጵያ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካዊያን ለመፍታት በቁርጠኝነት እየሠራች መሆኗን የመከላከያ ሚኒስትሯ ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ገለፁ።
as
ኢትዮጵያ እና ኮንጎ ሪፐብሊክ (ብራዛቢል ) በወታደራዊ መስኮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
s6
በአምባሳደር ጄነራል ባጫ ደበሌ የተፃፈው ''የፀረ-ሽምቅ ውጊያ ጥበብ'' መፅሐፍ ተመረቀ።
mf
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች አካል መሆን እንዳለባት የፈረንሣይ የምድር ኃይል አዛዥ ጄነራል ፒየር ሺል ገለፁ።
ay3
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ከኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።
Y
ፈረንሣይ ከኢትዮጵያ ጋር በወታደራዊ መስክ የበለጠ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን የፈረንሣይ ምድር ጦር አዛዥ ጄኔራል ፒየር ሺል ገለፁ።

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ