የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጷጉሜን 03 ቀን 2017 ዓ.ም
ለሁሉም የመከላከያ ሠራዊት የክብር አባላት፦
እንኳን ወደ አዲሱ ዓመት 2018 ዓ.ም በሰላምና በጤና አደረሳችሁ። ያለፈው 2017 ዓ.ም ከባድ የትግል ዓመት ነው መስዋዕትነት እየከፈልን እና እየከፈላችሁ ከውስጥና ከውጪ ሊያጠፋን ያሰፈሰፉትን ሃይሎች በፅናት ታግለን ያሸነፍንበት የድል ዓመት ነው። አሁን ወደ አዲሱ ዓመት በድል የተሻገርንበት የ2017 መጨረሻ ዓመት ላይ ነን።
ዛሬ ማታ ሕዳሴ ግድብ ላይ ሆኜ የፅናት ተምሳሌት ዜጎችን ሳስብ ለሕዳሴ ግድብ ስኬት ሲሉ ሕይወት የከፈሉትን አካላቸውን ያጎደሉትን ወታደሮችና የሕዳሴ ግንባታ ሲያከናውኑ የተሰውትን፤ ገንብተው ያሸነፉትን የሕዳሴ ግድብ ጀግና ሠራተኞችን ሁሉ በሕሊና ፀሎት አስታወስኳቸው። ጨክኖ ከኢትዮጵያ አገሩ ጋር የቆመውን፤ መቀነታቸውን ፈተው የሰጡ እናቶችን፤ በአጠቃላይ ግድቡን ለጨረሱ የኢትዮጵያ ሕዝብ ክብርና ምስጋና አቀርባለሁ።
አንዳንድ ዜጎች ተሽጠው ከጠላት ወግነው የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅሞች ሲያጠለሹ ሲያጣጥሉ ማህበራዊ ተፅዕኖ ሲፈጥሩ በነፍጥ አገር ሲያዳክሙ አገር ትወረር ሲሉ እናንተ የመከላከያ የክብር አባላት ግን በወገንተኝነት በደፋርነት በአገር ወዳድነት የጠላትን ማህበራዊ ተፅዕኖ ተቋቁማችሁ ያደረጋችሁት የትግል ታሪክ ተመዝግቦ ይኖራል።
ለዓመታት ለኢትዮጵያ ብላችሁ የጮሃችሁትን ጩኸት የያዘ ቪዲዮ ለልጆቻችሁ አስቀምጡና ታሪክ ስለሰራችሁ ልጆቻችሁ አያፍሩበትም። ፀረ ኢትዮጵያ የሰሩ ዜጎቻችንም የሰሩትን ፀረ ኢትዮጵያ ተልዕኮ ለልጆቻቸው ያሳልፉና ሁለቱም ልጆች ጎን ለጎን ቆመው የሁለታችሁንም ታሪክ ይተርኩ። ሁለት ትረካ ለቀጣይ ትውልድ ይቀርባል። የአርበኛና የባንዳ ማንነትን ነገ በታሪክ መነፀር ልጆች እንደሚያዩት አልጠራጠርም።
እንኳንም የክብር አባሎቻችን አደረግናችሁ መልካም አዲስ አመት፤ እንኳን አደረሳችሁ።
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
http://www.facebook.com/fdredefense.official
